1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን እና የዩሮ ማጠናከሪያ ስልትዋ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2003

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሄር እና መራህያነ መንግስት ዛሬ በብራስልስ የሁለት ቀናት ምክክር ይጀምራሉ።

https://p.dw.com/p/Qdhc
ምስል picture alliance / dpa

የጉባዔው ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ ዩሮን ለማረጋጋት የሚቻልበት ጉዳይ ነው። በርካታ የህብረቱ አባል ሀገሮች የፊናንስ እና የኤኮኖሚ ቀውስ እንዳይገጥማቸው ከሀብታሞቹ አባል ሀገሮች ብድር ጠይቀዋል። ህብረቱ ቀደም ባሉ ጊዜ ለግሪክ እና ለአየርላንድ ተመሳሳይ ርዳታ ማድረጉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ስጳኝ ርዳታ እንደምትፈልግ ነው የተሰማው። የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ትናንት በሀገራቸው ምክር ቤት በዩሮ ዙርያ ባሰሙት ንግግራቸው ዩሮን ለማጠናከር እና በቀውስ የተጎዱትን ሀገሮች ለመርዳት ጠንከር ያለ ደምብ እንዲወጣ አንጌላ ሜርክል ሀሳብ አቅርበዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሒሩት መለሰ