1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን የምትሰጠው የደም ካሳ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 29 2002

ሰሜናዊ አፍጋኒስታን ውስጥ ኩንዱስ በተባለው አካባቢ አቅራቢያ በጀርመን ጦር አዛዥ ትዕዛዝ ባለፈው ዓመት በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ ለደረሰው የቦምብ ድብደባ ሰለባዎች የደም ካሳ እንደሚሰጥ የጀርመን መንግስት አስታወቀ ።

https://p.dw.com/p/KxQk
ምስል AP

በዚሁ መሰረትም መንግስት ከሰለባዎቹ ቤተሰቦች ጠበቃ ጋር መነጋገር እንደሚጀምር የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግረዋል ። የጥቃቱ ሰለባዎች እና የቤተሰቦቻቸው ጠበቃ ካሪም ፖፓል ፣ ጀርመን ለሰባ ስምንት ቤተሰቦች የደም ካሳ እንድትከፍል ጠይቀዋል ። እንደ ጠበቃ ፓፓል የነሀሴው የቦምብ ድብደባ ሰለባዎች 179 ሰላማዊ ሰዎች ሲሆኑ ከመካከላቸው 137 ቱ ሲገደሉ 20 ቆስለዋል 22 ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ። ። ይሁንና በአየር ድብደባው የሞቱትን ሰዎች ቁጥር እንደሚያጣራ የገለፀው የጀርመን መንግስት ለአደጋው ሰለባዎችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ሶሶት ሚሊዮን ዩሮ ካሳ ሊከፍል ነው መባሉንም ግምት ነው ሲል አስተባብሏል ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ