1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጄኮብ ዙማ እና የተቀሰቀሰባቸው የሙስና ክስ

ማክሰኞ፣ ጥር 5 2001

የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዳስረዳው ከዚህ ቀደም በዙማ ላይ የተመሰረተው የሙስና ክስ እንዲሰረዝ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተላለፈው ውሳኔ ስህተትና መሰረታዊ ህጋዊ ደረጃዎችንም ያልጠበቀ ነበር ።

https://p.dw.com/p/GXkZ
ጄኮብ ዙማምስል picture-alliance/dpa
በደቡብ አፍሪቃ የፊታችን ሚያዚያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የአፍሪቃ ብሄራዊ ምክር ቤቱ መሪ ጄኮብ ዙማ በቀላሉ ድል እንደሚጎናፀፉ እስከትናንት ድረስ አንዳችም አጠራጣሪ ነገር አልነበረም ። ሆኖም ዙማ ያለ መሰናክል ማሸነፍ መቻላቸው እንዲያውም ከነአካቴው ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር መብቃታቸው ከትናንት አንስቶ ማነጋገር ጀምሯል ።