1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ገንዘቤ ዲባባ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 6 2006

ፈጣን ፣ደፋር እና ወጣት አትሌት ናት። ገንዘቤ ዲባባ። የ23 ዓመቷ ወጣት ወደ ሩጫው ዓለም ከገባች 8 ዓመታት ተቆጠሩ።

https://p.dw.com/p/1BPSJ
Genzebe Dibaba Sopot World Indoor Championships 09.03.2014
ምስል picture-alliance/dpa

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፖላንድ በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዎና የ3000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ፤ በጠቅላላው የ5 ወርቅ እና የአንድ ብር ሜዳልያ ባለቤት ናት፤ ወጣት -አትሌት ገንዘቤ ዲባባ። እሷም እንደ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊ ሯጮች የተወለደችው አርሲ ነው። ገንዘቤ ወደ አዲስ አበባ የሄደችው በሥራ ምክንያት መሆኑን ገልፃልናለች።

እሷና ሌሎች አብረዋት የሚሰለጥኑት አትሌቶች በቀን ሁለት ጊዜ ይለማመዳሉ። ዕረፍት ግዴታ ቢሆንም ስፖርት ሱስ ሆኖባታል።የጥሩነሽ እና የእጅጋየሁ ዲባባ እህት የሆነችው ገንዘቤ ከሁለቱ ታዋቂ ራጭ እህቶቿ በተጨማሪ ሌሎች ራጮችም በቤተሰቧ ይገኛሉ።ገንዘቤ እውቅናና ዝና ያተረፉ እህቶች ቢኖሯትም በግሏ ጠንክራ ለራሷ ውጤት የምትታገል እንደሆነች ይነገርላታል።በረፍት ጊዜዋ ዋና መዋኘት እና ብስክሌት መንዳት ትወዳለች።ወጣቷ ስለ የፍቅር ህይወቷም አውግታናለች።

የመካከለኛ እና የአጭር ርቀት ራጭ የሆነችው አትሌት ገብዘቤ ዲባባን ከዶይቸ ቬለ ጋር የነበራትን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ