1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ገጣሚ ማርታ ሐይለእየሱስ

ዓርብ፣ መጋቢት 21 2004

ማርታ ሐይለእየሱስ በትርፍ ጊዜዋ ግጥም መግጠም የምታዘወትር ወጣት ነች። ከፃፈቻቸው ግጥሞች ሁለቱን ይዛ በዛሬው የወጣቶች ክፍለ ጊዜ አብራን አምሽታለች። ማርታ ሐይለእየሱስ በትርፍ ጊዜዋ ግጥም መግጠም የምታዘወትር ወጣት ነች።

https://p.dw.com/p/14VDa
ምስል Fotolia/silver-john

ማርታ ግጥሞቿ በተለያዩ ጭብጦች ላይ እንዳተኮሩ ትናገራለች። ለምሳሌ በፍቅር፣ በሀገር፣ በማህበራዊ ነገሮች ላይ እና በሌሎችም ርዕሶች ላይ፤ እሷም እንደገጣሚ እነዚህ ጉዳዮች ወሳኝ ናቸው ትላለች። ማርታ እስካሁንም ከ50 የሚበልጡ ግጥሞች ፅፋለች።

የ24 ዓመቷ ማርታ ግጥም የመፃፍ ፍላጎቱና ዝንባሌው ያላቸው ወጣቶች ይህንኑ ችሎታቸውን ለማዳበር ጠንክረው ቢሰሩ መልካም እንደሚሆን ታምናለች። እንደሷ ግጥምን በት/ቤት ብቻ ሳይሆን በትርፍ ሰዓታቸውም እንዲፅፉ እና የቋንቋ ችሎታቸውን በት/ቤት እንዲያሳድጉም ትመክራለች። ይህንን አላማቸውን ከግብ ለማድረስ መደረግ ይኖርበታል ስለምትለው ማርታ ታስረዳለች። ከግጥሞቿ ሁለቱን እንዲሁም ከኢትዮጵያዊ የቀድሞ እና ያሁን ገጣሚያን የማን አድናቂ እንደሆነች ጭምር የገለፀችልንን ማድመጥ ይቻላል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ