1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዘጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 23 2004

መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት CPJ በጋዜጠኛ ተመስገን መለቀቅ መደሰቱን አስታውቆ ሌሎች የታሰሩ ጋዜጠኞችም እንዲፈቱ ጥሬ አቅርቧል ።

https://p.dw.com/p/15zXZ
Eine Statue der Justitia, Göttin der Justiz und der Gerechtigkeit, steht auf dem Gerechtigkeitsbrunnen auf dem Frankfurter Römerberg und hält eine Waage mit zwei Waagschalen in der Hand, fotografiert am 15.02.2008. Foto: Wolfram Steinberg +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa



የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በተመስገን ደሳለኝ ላይ መሥርቶት የነበረዉን ክስ መቋሩጡን የመንግሥት ባለሥልጣናት አስታወቁ።ጋዜጠኛ ተመስገን በቅርቡ አመፅና ሁከት የሚቀሰቅስ ዘገባ አዘጋጅቷል የሚል ክስ ተመስርቶበት ባለፈዉ ሐሙስ ታስሮ ነበር።ትናንት ተለቋል።የተመሰረቱበት 3 ክሶችም መቋረጣቸው ተነግሯል ተመስገን የተለቀቀበትን ምክንያት በትክክል አያዉቀዉም።የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል እንዳስታወቁት ግን አቃቤ በተመስገን ላይ የመሠረተዉን ክስ የሠረዘዉ ወይም ያቋረጠዉ ሐገሪቱ መሪዋን በሞት አጥታ ሕዝቡ ሐዘን ላይ በመሆኑ ነዉ።ተመስገን በዋና አዘጋጅነት የሚመራዉ የፍትሕ ጋዜጣ የተወሰኑ እትሞች እንዳይሰራጩ፥ ያልታተመዉ ደግሞ እንዳይታተም ታግዶም ነበር።የጋዜጣዉ ቅጂ አለመታተሙና የተመስገንን መታሰር የተለያዩ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ተቋማት አዉግዘዉት ነበር።መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት CPJ በጋዜጠኛ ተመስገን መለቀቅ መደሰቱን አስታውቆ ሌሎች የታሰሩ ጋዜጠኞችም እንዲፈቱ ጥሬ አቅርቧል ።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ