1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዛ፤ የእስራኤል ወታደር መታገትና አፀፌታው

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 26 2006

አንድ እስራኤላዊ ወታደር ጋዛ ሠርጥ ውስጥ ሳይታገት አልቀረም መባሉን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ከባድ የተሰኘ የአፀፋ ጥቃት መሰንዘሩ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1CnwT
Nahostkonflikt Gazastreifen 2.8.2014
ምስል Reuters

እጅግ ብርቱ እንደሆነ በተነገረለት የዓየር ኃይል ጥቃት ደቡባዊ ጋዛ ሠርጥ ውስጥ ከትናንት አንስቶ ከ100 በላይ ፍልስጥኤማውያን መገደላቸው ተዘግቧል። ከአርብ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ይዘልቃል ተብሎለት የነበረው የተኩስ አቁም የተጣሰው ተኩስ ማቆሙ ከተነገረ ሁለት ሠዓታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። የተኩስ አቁሙ ለመጣሱ ሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት ማለትም የእስራኤል ጦር እና የሐማስ ቡድን እርስ በእርስ ተወነጃጅለዋል። የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ጊሙን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የታገተው የእስራኤል ወታደር፤ ኮሎኔል ሐዳር ጎልዲን በአስቸኳይ እንዲለቀቅ ጥሪ አስተላልፈዋል። ታጣቂው የሐማስ ቡድን ስለታገተው እስራኤላዊ ወታደር ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ይፋ አድርጓል። ምናልባትም ታገተ የተባለው እስራኤላዊ ወታደር ሳይገደል እንዳልቀረ ኤዘዲን ኧል ቃሳም ብርጌድ የተሰኘው ቡድን አስታውቋል። ከእስራኤል አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ የእስራኤል ወታደሮች የመሬት ውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ ጉድጓዶችን ሲደረምሱ በአንድ አጥፍቶ ጠፊ ሁለት የእስራኤል ወታደሮች ከተገደሉ በኋላ ኮሎኔሉ ሳይታገድ እንዳልቀረ ተገምቷል። የፍልስጥኤም ሚሊሺያዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ሲያስወነጭፉ እንደነበር ተዘግቧል። እስካሁን ድረስ በእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት ቢያንስ 325 ፍልስጥኤማዊ ሕፃናት መገደላቸው ተጠቅሷል። ከ2000 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ