1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኝነት በግጭት አካባቢዎች

ማክሰኞ፣ ግንቦት 25 2001

የፕሬስና የመገናኛ ብዙሀን ነፃነት የአንዲት ሀገር ዲሞክራሲያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ዕድገት መሰረት ሲሆን የህዝብ ንብረትም ተደርጎ ነው የሚወሰደው ። ከስድስት ዓመት በፊት የዓለም ባንክ “የመንገር መብት” በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ ላይ በልማት ዕንቅስቃሴ ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ያላቸውን ቁልፍ ድርሻ አጉልቶ አስቀምጧል ።

https://p.dw.com/p/I2Fr
ምስል dpa

ይሁንና ቀውሶችና ግጭቶች በሚካሄዱባቸውና በተካሄዱባቸው ሀገራት በፕሬስ ነፃነት ውስጥ ግጭቶችን የማያባብስ ይልቁንም መፍትሄው ላይ የሚያተኩር ሀለፊነት የተሞላበት ጋዜጠኝነት ያስፈልጋል ። እዚህ ላይ ነው ግጭቶች እንዳይባባሱ የሚረዳ ጋዜጠኘት ፅንሰ ሀሳብ ተግባራዊ መሆን የሚገባው ። በዚህ መሰረት የሚዘግቡ ጋዜጠኞች እንደሚናገሩት ይህ ወቅት አመጣሽ መፈክር ሳይሆን በጣም ለየት ያለ የጋዜጠኝነት መንገድ ነው ። ሞኒካ ሆገን የዘገበችውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ሞኒካ ሆገን/ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ