1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ጋዝፕሮም»ና ነዳጅ ዘይት ፍለጋ በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 22 2006

የዓለም አቀፉ የ «ጋዝፕሮም » ኩባንያ ባንክ (GPB Global)በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በአፋር መስተዳድር፤ ነዳጅ ዘይ ት ለመፈለግ ከአንድ ወር ገደማ በፊት ውል መፈራረሙ ተመልክቷል።በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ዘይት አሳሽ ኩባንያዎች፣ እስካሁን

https://p.dw.com/p/1D3LH

የተሣካ ውጤት ያለማግኘታቸው ምክንያቱ ምን ይሆን? የውጭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ንዘባቸውን ሥራ ላይ ማዋል ይችሉ ዘንድ አማላዩ ሁኔታ ምን ይመስላል?ገንዘብ ሥራ ላይ የሚያውሉ ኩባንያዎችን ከሚያማክሩ ድርጅቶች መካከል፤ ሶኮኒ የተሰኘውን ኩባንያ ተጠሪ አነጋግረናል።

Themenheader Energie
ምስል Fotolia

የጋዝ ፕሮም ዓለም አቀፍ ባንክ የመገናኛ ክፍል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰርጌይ ታጋሾቭ፣ በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ፤ ለ 7 ዓመታት በ 42 ሺ ካሬ ኪሎሜትር ቦታ አሰሳና ቁፋሮ ለማካሄድ ፣ ብሎም ለ 25 ዓመታት የሚገኘውን ሃብት ለመካፈል ስምምነት ላይ መደረሱን ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ ፤ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል እንደተባለው 4 ትሪሊዮን ኩብ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ከምችት አላት ሆኖም እስካሁን አውጥታ ጥቅም ላይ ያዋለችው ተመሳሳይ የተፈጥሮ ሀብት የለም። በአፋር ምድር ነዳጅ ዘይት ለማግኘት ያለው ብሩሕ ተስፋ እስከምን ድረስ ይሆን? የውጭ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ሥራ ላይ እንዲያውሉ የሚያግባባና የሚያማክር መሆኑን የሚገልጸው «ሶኮኒ» የተሰኘው አማካሪ ድርጅት የአስተዳደር መሪ ማርክ ሼፓርድ--

«የሥነ ቴክኒክ አማካሪ ባለመሆኔ በቀጥታ ይህ ነው ብዬ ትክክለኛ ግምት ለመስጠት እቸገራለሁ። ይሁንና ለነዳጅ ፈላጊዎች በጎውen ነው የምመኝላቸው። መንግሥት 14 ገደማ ለሚሆኑ የጋዝ ፈላጊ ኩብንያዎች አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል። ውጤት ካገኙ በኋላም፤ ኩባንያዎቹ ገንዘብ በዚያው ሀገር ይበልጥ ሥራ ላይ እንዲያውሉ ተስማሚ ደንቦችን አውጥቷል። ማንኛውም የማዕድን ግኝት ለኢትዮጵያ ጠቀሜታ አለው።በዚህ ዘርፍ፣ ገንዘብ ፣ መንግሥት እጅ እስኪገባ፣ ረጅም ጊዜ ይወስዳል ።ማንኛውም ማዕድን የማውጣት ተግባር ፣ ወደ ውጭ ለገበያ ማቅረብ የሚቻልበትን የረጅም ጊዜ ስልት ማውጣትን ይጠይቃል። ይህም ትልልቅና ረጃጅም የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችን መዘርጋትንም ያጠቃልላል»።

Äthiopien Wüste Danakil
ምስል picture-alliance/dpa

ታላቁ ስምጥ ሸለቆ ፣ ነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ እንደሚገኙበት ፤ ከላይ ሰሜን የመንን ከደቡብ ደግሞ ፤ አዲሶቹ ን የነዳጅ ዘይት ባለጸጎች ኬንያንና ዩጋንዳን መጥቀስ ይቻላል ፤ ከጎን ደግሞ ደቡብ ሱዳን አለች። ከታች የአዋሽን ወንዝ ተከትሎ በመስኖ ከሚካሄድ ልማት ሌላ ምድረ በዳ ቀመስ በሆነው የአፋር ምድር ፤ የጨው፣ የድኝና ፖታሲየም ማዕድናት እንደሚገኙ የታወቀ ነው። ግን ነዳጅ ዘይት የሚገኝበት ምልክት ተገኝቷል ወይ?

«እንደገና በዚህም ላይ ትክክለኛ ግምት ለመስጠት ይከብደኛል። ግን ፤ ይህ ላገሪቱ የሚያስፈልግ ማዕድን መሆኑ ከቶ አያጠያይቅም። እርግጥ ጋዝፕሮም፣ በትጋት ሥራውን ተያይዞታል። የነዳጅ አሰሳ፤ በመጀመሪያ አድካሚ ነው። እንደሚታሰበው ሁሌ የፈለግኸው ነገር አይገኝም።

Russland Logo von Gazprom in Moskau
ምስል picture-alliance/dpa

ይሁንና ማዕድኑ፣ ነዳጅ ዘይቱ ከተገኘ፣ አካባቢው በባህር መሥመር ላይ በመሆኑ ፤ ወደ ውጭ ለገበያ ማቅረብ የሚቻልበትን መንገድ ቀላል ያደርገዋል። ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ ጥቅም ሲታሰብ ኪሣራም ሊያጋጥም የሚችልበት ሁኔታ አለ። ዘይቱ ቢገኝም፣ የሚፈለገው ያህል እሚገኝበት ቦታ ላይ ባለመቆፈር ድካም ነው የሚያስከትለው።»

ኢትዮጵያ ፤ የደቡብ ሱዳን ጎረቤት ናት፣ ኬንያ ከደቡብ ዩጋንዳም በተመሳሳይ መሥመር ነው የምትገኘው። አነዚህ አገሮች ሰፊ የነዳጅ ዘይት ሀብት አላቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆነበት ምክንያት ምን ይሆን? ነዳጅ ፈላጊዎቹ አልሆነ ቦታ እየቆፈሩ ነው ወይስ--

Themenheader Energie
ምስል Fotolia

«እንደሚመስለኝ የአፈርና ቋጥኝ ባለሙያዎችን ማነጋገር ሳይሻል አይቀርም። አፈሩ፤ ቋጥኙ የተለዬ ነው። ከደቡብ ሱዳንና ኬንያ የተለዬ ነው። ግን ያን ያህል ከኦሞ ወንዝ አካባቢመሬት የተለየ አይደለም። »

የጋዝ ፕሮም የመገናኛ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰርጌይ ታጋሾቭ፤ በበኩላቸው በምሥራቅ አፍሪቃው ሥምጥ ሸለቆ፣ የተለያዩ አገሮች ነዳጅ ዘይት ማግኘታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያም እንደማታጣ ነው በስላች የተናገሩት። እርሳቸውና ማርክ ሼፓርድ እንደሚሉት፤ ለልማት ሥራ ማንቀሳቀሻና የንግድ መዛባትን ለማስተካከያ የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ የገቢ ምንጭ ይሆናል ብሎ ትኩረት የሰጠው ለማዕድን የማውጣት ተግባር ነው። በቅርቡ ዋና ጽ/ቤቱ በለንድን የሚገኘው Tullow Oil የተሰኘው ነዳጅ አሳሽ ኩባንያ፤

NO FLASH Symbolbild Erdölförderung
ምስል picture alliance/dpa

በደቡባዊው ኢትዮጵያ ነዳጅ ለማውጣት ለ 4ኛ ጊዜ ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ፤ ሆኖም የማሰሱን ተግባር እንደሚገፋበት ፤ የኩባንያው ዋና ጸሐፊ ጆርጅ ካዘኖቭ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። የጋዝ ፕሮም ባንክ የመገናኛዎች ጉዳይ ኀላፊ ታጋሾቭ፣ ከሳምንታት በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት፣ በአፋር ምድር የነዳጅ ዘይት ፍለጋው ቅኝት በ 3 ወራት ውስጥ ይጀመራል። ግኝቱ ፣ ወደ ውጭ ለማቅረብ የሚያስችል ትልቅ ቧንቧ መዘርጋት ባያስችልም፣ የአገር ውስጡ ምርት ሽያጭ ዋጋው እንዲከፈል ያስችላላልም ብለዋል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ