1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጌታቸው ተድላ በአሜሪካ ቆይታው ወቅት ያስተላለፈው ዘገባና ቃለምልልስ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 1997

ባለፉት ጥቂት ሣምንታት ውስጥ ለሥራ ጉዳይ ዩኤስ-አሜሪካ ውስጥ የሰነበተው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ እዚያው ከአንዱ ቦታ ወደሌላው ሲዘዋወር በቆየበት ወቅት፣ በልይዩ የግል ሥራ መስኮች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሮ ነበር።

https://p.dw.com/p/E0f5

በዚያችው ግዙፍና ሐብታም ሀገር ውስጥ በግለሰብእ ደረጃ ስላለው የሥራና የዕድገት ዕድል፣ ምሁራኑ ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው የውዒሎተንዋይ ተሳትፎ ሊያደርጉ ስለሚችሉበትም ሁኔታ ነበር ውይይት ያካሄደው ። ከእነዚሁ መካከል በተለይ አርአያ ሆነው ካያቸው ከአቶ ሰሎሞን በቀለ ጋር በቨርጂኒያ/አለክሳንድሪያ ሰፊ ቃለ ምልልስ ነበር ያደረገው። ዛሬ የምንመለከተው፥ ጌታቸው ተድላ ከዚያችው ያልተገደበ ዕድል ያለባት ሀገር ከምትባለው ዩኤስኤ የራሱንም ሐተታ በማከል ያስተላለፈልንን ይህንኑ ቃለምልልስ ነው። ሐተታውንና ቃለምልልሱን እነሆ ከዚህ ቀጥሎ በዌብሳይቱ ማዳመጥ ይቻላል።