ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ
ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2008ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ልዩ ልዩ ችግሮች ለመፍታትና በሃገሪቱም እርቀ ሰላም ለማውረድ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ ። የመግባባት አንድነትና ሰለም ማህበር የተሰኘው ሃገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጉዳዩ ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጠው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በዚህ ሳምንት በላከው ግልፅ ደብዳቤ ጠይቋል ። ደብዳቤው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከው አዲሱ ካቢኔ በዚህ የሃገር ጉዳይ ላይ እንዲወያይና ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዩ ላይ ከህዝቡ ጋር እንዲመክሩበት ለመሳሳበብ መሆኑን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።አቶ ፋንታሁን እንዳሉት የማህበሩ ደብዳቤ እስካሁን መልስ አላገኘም።ስለ ደብዳቤው ዶቼቬለ የጠየቀው የመንግሥት ኪሚኒኬሽን ሚኒስቴር ፣ደብዳቤው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት አልደረሰም ብሏል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ