1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግሪክና የአዉሮጳ ቀዉስ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 23 2007

የግሪክ እና የአበዳሪዎችዋ መንግሥታትና ተቋማት ባለሥልጣናት ሥለ ብድር አሰጣጥ፤ ዕዳ ክፍያና ገቢ አሰባሰብ ለአምስት ወራት ያደረጉት ድርድር ያመጣዉ ዉጤት የለም።የግሪክ ሕዝብ አበዳሪዎች ያቀረቡትን ቅድሜ ግዴታ መደገፍ መቃወሙን በድምፁ እንዲወስን የሐገሪቱ መንግሥት ለመጪዉ ዕሁድ ሕዝበ-ዉሳኔ ጠርቷል

https://p.dw.com/p/1FqBW
ምስል Getty Images/M. Bicanski

[No title]

ግሪክ ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እስከ ዛሬ አኩለ ሌት ድረስ መክፈል የሚገባትን 1,6 ቢሊዮን ዩር ዕዳ መክፈል እንደማትችል የሐገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።ግሪክ ዕዳዉን የማትከፍለዉ አበዳሪ መንግሥታትና ተቋማት ተጨማሪ ብድር ሥላልሰጥዋት ነዉ።የግሪክ እና የአበዳሪዎችዋ መንግሥታትና ተቋማት ባለሥልጣናት ሥለ ብድር አሰጣጥ፤ ዕዳ ክፍያና ገቢ አሰባሰብ ለአምስት ወራት ያደረጉት ድርድር ያመጣዉ ዉጤት የለም።የግሪክ ሕዝብ አበዳሪዎች ያቀረቡትን ቅድሜ ግዴታ መደገፍ መቃወሙን በድምፁ እንዲወስን የሐገሪቱ መንግሥት ለመጪዉ ዕሁድ ሕዝበ-ዉሳኔ ጠርቷል።ባርባራ ቬዘል የፃፈችዉን ሐተታ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ ተጉሞቶታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ