1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብጽና የተሃድሶ ጥረት

እሑድ፣ የካቲት 6 2003

በግብጽ የሆስኒ ሙባራክ ከሥልጣን መሰናበት የአገሪቱን ሕዝብና ሰፊውን ዓለም እጅግ አስደስቷል። አገሪቱን ለሰላሣ ዓመታት የገዙት የቀድሞ መሪ 18 ቀናት ከፈጀ ሕዝባዊ የአደባባይ ግፊት በኋላ ካይሮን ጥለዉ ሻርም-ኤል-ሼይክ መኖሪያቸው እንደተሸሸጉ እየተገለጸ ነዉ።

https://p.dw.com/p/R0S1
ምስል dapd


በሌላ በኩል ሆስኒ ሙባረክ በስዊዘርላንድ ባንክ በራሳቸዉንና በዘመዶቻቸዉ ስም ያካማቹትን በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የስዊዝ ባንክ ማገዱ ተነግሮአል። የግብጽ ሕዝብ አምባገነን ገዢውን አስወግዶ ትናንት አንድ ብሎ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሲከፍት ለአስራ ስምንት ቀናት አደባባይ ውሎ አድሮ ተቃዉሞ ያሰማበትን አደባባይ በመጥረግ እና በማሳመር ነዉ።