1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብፃዊቷን የገደለዉ ተፈረደበት

ረቡዕ፣ ኅዳር 2 2002

ድሬዝደን ያስቻለዉ ፍርድ ቤት-ገዳዩን አሌክሳንደር ቪየንስ ለግድያዉ ሙሉ በሙሉ ጥፈተኛ አድርጎታል።

https://p.dw.com/p/KU4t
ገዳዩ ፍርድ ቤትምስል AP

ምሥራቅ ጀርመን ዉስጥ ባለፈዉ ሰኔ ማብቂያ አንዲት ግብፃዊት ነብሰ ጡር ወይዘሮን ፍርድ ቤት አዳራሽ ዉስጥ በጩቤ ጨቅጭቆ የገደለዉ ጀርመናዊ ወጣት ዛሬ እድሜ ልክ እስራት ተበየነበት።የሃያ-ስምንት አመቱ ወጣት ግብፃዊቱን ወይዘሮ በገደለበት ወቅት ባለቤቷንም አቁስሎ ነበር። ግድያዉና የጀርመን መንግሥት ፈጥኖ ግድያዉን አለማዉገዙ ከፍተኛ ቁጣና ተቃዉሞ አስከትሎ ነዉ የሰነበተዉ።ዛሬ ድሬዝደን ያስቻለዉ ፍርድ ቤት-ገዳዩን አሌክሳንደር ቪየንስ ለግድያዉ ሙሉ በሙሉ ጥፈተኛ አድርጎታል።ፍርዱ ከመሰጡት በፊት ሥለ ሒደቱ የበርሊን ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ/ይልማ ሐይለ ሚካኤል
አርያም ተክሌ