1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግንቡ ሲፈርስ የነበሩ ኢትዮጵያያን ትውስታ

ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2002

ልክ የዛሬ ሀያ ዓመት በዛሬዋ ዕለት በርካታ ጀርመናውያን ያላሰቡት ነገር ግን የዘወትር ምኞታቸው የነበረ እና እስከዛሬም እንደ ተዓምር

https://p.dw.com/p/KTEI
ምስል AP

የሚቆጥሩት ነገር እውን ሆነ ። ጀርመንን ለሁለት ከፍሎ የቆየው የበርሊን የግንብ አጥር ፈረሰ ። የዚህ አጥር መናድ ለሁለቱ ጀርመኖች ውህደት መንገድ በመጥረግና በዓለም ዙሪያ የኮምኒዝምን ስርዓት መንኮታኮት በማፋጠን በዓለም ታሪክ ልዩ ቦታን ይይዛል ። ይህ ዕለትም ዛሬ በርካታ የዓለም መሪዎች በተገኙበት በዋና ከተማይቱ በበርሊን እየተከበረ ነው ። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የዛሬ ሀያ ዓመት የሆነውን ወደ ኃላ መለስ ብሎ ያስቃኘናል ። ግንቡ ሲፈርስ የነበሩ ኢትዮጵያያን ትውስታቸውን ያካፍሉናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ