1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጡት ማብራሪያ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 2 2001

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጡ።

https://p.dw.com/p/GDrc
ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ
ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊምስል AP Photo

ብዙዎቹ ጥያቄዎች በሶማልያ፡ ብሎም፡ የኢትያጵያ መከላከያ ሰራዊው ከዚያ ይወጣል በተባለበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነበሩ፤ ይሁንና፡ በርካታ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ፡ ለምሳሌ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና መገናኛ ብዙኃን መንግስታቸውን አዘውትረው የሚወቅሱበት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ፡ የፊናንሱ ቀውስ፡ የምግብ ዋጋ ንረትና ግሽበትን የመሳሰሉ ጥያቄዎችም ተነስተው ነበር። ታደሰ እንግዳው