1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊና የቡድን 8 ጉባኤ

ዓርብ፣ ግንቦት 10 2004

ዩናይትድ ስቴትስ ካምፕ ዴቪድ ዉስጥ በሚካሄደው የቡድን 8 ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የውይይቱ ተካፋይ እንዲሆኑ መጋበዝ ልክ አይደለም በማለት ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገተው የጀርመን ድርጅት መጨረሻ ጋዜጣዊ መግለጫ አዉጥቷል።

https://p.dw.com/p/14vqx
Die Farm von der Größe Luxemburgs des indischen Agrarmultis in der Gambella-Provinz
ምስል DW

የኢትዮጵያ መንግስት ለውጭ ሀገር ድርጅቶች እና ባለሀብቶች መሬት በሊዝ የሚሰጥበት ፖሊሲ ትክክል አለመሆኑን ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገት አንድ የጀርመን ድርጅት ባለፈው አርብ ባወጣው የፕረስ መግለጫ ገልጿል። በዚሁ ሰባት በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ምዕራብ አገራት እና ሩሲያ በሚካፈሉበት  የቡድን 8 ጉባኤ ላይ ከአፍሪቃ ከተጋበዙት አራት መሪዎች መካከል ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አንዱ ናቸው። የዮናይትድ እስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጉባኤው ላይ ከአፍሪቃውያኑ መሪዎች ጋ በአህጉሩ በየጊዜው የሚከሰተውን ረሀብና የምግብ እጥረትን መታገል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገተው የጀርመን ድርጅት ተጠሪ ኡርሊሽ ዴሊዎስ ይህንኑ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሀገራቸው በሚከተሉት የመሬት ይዞታ የተነሳ በካምፕ ዴቪዱ ጉባዔ ላይ አፍሪቃን ወክለው ሊናገሩ አይችሉም።

epa03026163 Meles Zenawi, Prime Minister of Ethiopia speaks during the opening plenary session of the High Level Segment of the COP 17 / CMP 7 United Nations (UN) Climate Change Conference 2011 in Durban, South Africa, 06 December 2011. The 17th session of the Congress of the Parties (COP) comprising 194 countries meeting to discuss the United Nations Framework Convention on Climate Change (UNFCCC) began its High Level Segment serving as the meeting of the Parties to the Kyoto Protocol. EPA/NIC BOTHMA
የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊምስል picture-alliance/dpa

« ፕሬዚዳንት ኦባማ በዚህ ጉባኤ ላይ በአፍሪቃ የምግብ ዋስትና ላይ ስለሚታየውም ችግር መወያያታቸው አይቀርም። እና በውይይቱ እንዲሳተፉ መለስ ዜናዊን ጋብዘዋል። እኛ ይህን ትክክለኛ ያልሆነ መልዕክት አድርገን ነው የምንመለከተው። ምክንያቱም በእኛ ዓይን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአፍሪቃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሳይሆን የቆሙት ለተቃራኒው፣  ብሎም በ10ሺ ለሚቆጠሩ ገበሬዎች ውድቀት ናቸው።  እና ይህ ትክክለኛ አካሄድን አያመላክትም።

ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገተው ድርጅት ያወጣው ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጠቅሶ እንደገለፀው፣ በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስን ያክል ስፋት ያለው መሬት ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች ዝግጁ ተደርጓል። ግን የድርጅቱ ተጠሪ ዴሊዮስ እንደሚሉት፣ ይህ መሬት ሕዝብ የማይገለገልበት ባዶ መሬት ሳይሆን ከ100 000 የሚበልጥ የአባባቢው ህዝብ የኑሮ መሰረቱን የገነባበት ነው ሲሉ አሰራሩን ነቅፈውታል። እና ቡድን 8 በዚሁ የመሬት ፖሊሲ አኳያ  ሊወስደው ይገባል ያሉትን ርምጃ ሲያብራሩ፤

«መለስ ዜናዊ በሀገራቸው የሚከተሉት የግብርና ፖሊሲ ውጤት በ10 ሺ ለሚቆጠሩ አነስተኛ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ እንዲጠየቁበት እንፈልጋለን። ይህ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ስለሚታየው  የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተለይም በመገናኛ ብዙኃን ላይ በሚወስዱት ጠንካራ ርምጃ፣ እና የኢንተርኔት አምደኞችን ፣ጋዜጠኞችን በሚያስሩበት አሰራራቸውም እንዲጠየቁበት እንፈልጋለን።  እና እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮች በፍፁም በቸልታ ሊታለፉ አይገባም።  ካለበለዚያ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሀገሮች ተአማኒነታቸውን ያጣሉ።» 

Gute Aussichten. Agromulti Karuturi, der bereits mit dem Anbau und Export von Schnittblumen in Äthiopien erfolgreich sind, will nicht zuletzt dank der Gambella-Farm zum "größten Nahrungsmittelhersteller der Welt" werden. Kritiker sagen, dass die 300.000-Hektar-Pacht nur dazu diene, den Aktienkurs des Konzerns an der Börse in Mumbai die Höhe zu treiben. Das würde auch die Deutsche Bank freuen, die Anteile besitzt. Copyright liegt bei Ludger Schadomsky/DW Aufnahmedatum für alle Fotos: 13.8.2011
የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያምስል DW/Schadomsky

ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ሺህ ሄክታር የሚቆጠር መሬት ለህንድና ለሳውዲ አረቢያ ባለሀብቶች እንደተሰጠ ይታወቃል። ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የአፍሪቃ ሀገሮች ከእነዚህ ሁለት የእስያ አገሮች ጋ ባደረጓቸው  ስምምነቶች፣ ከአፍሪቃውያቱ ሀገሮች ጋ በአጋርነት እንደሚሰሩ እና ሁለቱም ወገኖች  ትርፋማ የሚሆኑበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ይናግራሉ። እና ባለሀብቶቹ ወደ አዳጊ አገሮች ሄደው ገንዘባቸውን በሚያሰሩበት ጊዜ፤ በርካታ የግብርና መሳሪያዎች ወደ አገሪቱ ሊገቡና የስራ ዕድል የሚፈጠርበት አጋጣሚም ሊኖር እንደሚችል የሚሰማው ሀሳብ ስህተት አለመሆኑን ኡርሊሽ ዴሊዎስ ቢናገሩም በተግባር እየታየ ያለው ሁኔታ የተለየ መሆኑን ነው የገለጹት።

« በርግጥ ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት አሰራር ኖሮ ቢሆን ኖሮ እኛ ሁኔታውን አንቃወመውም። ግን ኢትዮጵያ  ለአንድ ሔክታር መሬት በአመት 90 ሳንቲም ብቻ ካገኘች ትርፏ ምኑጋ እንደሆነ አይገባንም። እና መሬትን ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች የማከራየቱ ሁኔታ አንዳችም ትርፍ አያስገኝም። እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ይህ አሰራር ለአጠቃላይ የሀገሪቱ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት ማለትም ኤክስፖርቱን የሚጠቅም እና  የአካባቢውን ህዝብ ኑሮ ማሻሻል መቻሉን ማሳመኛ አላቀረበም።  ስለሆነም ይሄ ሰፊ መሬትን ለውጭ ባለሀብቶች የማከራየቱ ፖሊሲ ሁኔታ የተሳሳተ አካሄድ ሆኖ እናየዋለን።»

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ