1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማስፋፋት የመምህራንና በኢንተርኔት የሚቀርቡ የምርምር ጽሑፎች ድርሻ፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 5 2002

ድህነትን በአመዛኙ ለመቅረፍ፣ የሀገር ሁለንተናዊ ግንባታን ለማስፋፋት ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑ ይታመንበታል።

https://p.dw.com/p/Oit8

እርሱም የሚንቀሳቀሰው በዚሁ ዘርፍ በሰለጠኑ ወይም በተማሩ መምህራን ነው። ኢትዮጵያን ለመሰለ አዳጊ ሀገር፤ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ምሁራን ሰፊና ገንቢ ድርሻ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ የሚያጠራጥር አይደለም። የትምህርት መዳረሱን ከዓላማዎቹ አንዱ ያደረገው የዓእማቱ የልማት ግብ፤ የቀረው ጊዜ 4 ዓመት ከ 5 ወር ገደማ ሲሆን፤ በዚህ ጊዜ ውስጥና ከዚያም በኋላ ለትምህርት መስፋፋት ፤ መምህራን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴ አማካንነት ምን ዓይነት አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይችላሉ? ከዓእማቱ የልማት ግብ አኳያም ሆነ ከዚያ ውጭ በአጠቃላይ ፤ በኢትዮጵያ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲስፋፋ የሚያስፈልጉት ምንድን ናቸው? አድማጮቻችን ፤ በተለያዩ ክፍለ ዓለማትና ሀገራት፤ በእስያ ፤ አውሮፓ እንዲሁም አፍሪቃ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፤ ለዶክተርነት ማዕረግ የሚያበቃ ምርምር የሚያደርጉ ወጣቶችንና ጎልማሶችን የሚያስተምሩትንና የሚያማክሩትን ፤ አሁን 40 ሺ ገደማ ተማሪዎች፣ በአመዛኙም የሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ተማሪዎች በሚገኙበት የስዋኔ(ፕሪቶሪያ) ዩኒቨርስቲ፣ ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶ/ር ማሞ ሙጬን አነጋግረናል።

(ድምፅ)----

ተክሌ የኋላ