1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማስፋፋት ፤

ረቡዕ፣ ነሐሴ 12 2002

በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራቻን፤ ባለፈው ሳምንት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማስፋፋት ፤ የመምህራንና በኢንተርኔት የሚቀርቡ የምርምር ጽሑፎች ድርሻ ፤

https://p.dw.com/p/OqsK
ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማስፋፋት ፤
እስታንፈርድ ዩኒቨርስቲምስል flickr/wallyg

ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማስፋፋት ፤

በሚል ርእስ ፣ ከፕሮፌሰር ዶ/ር ማሞ ሙጬ ጋር ካደረግነው ቃል ምልልስ የመጨረሻውን ክፍል እናቀርባለን። በቅድሚያ ግን ሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ቀመስ ዜና--

በዩናይትድ እስቴትስ የመስማት ችግር የተደቀነባቸው ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣት ተማራማሪዎችን አስደነገጠ። ዕድሜአቸው በ 12 እና 19 ዓመት እርከን ላይ የሚገኝ ፤ ከየ 5ቱ አሜሪካዊ አንዱ ወጣት (ከሞላ ጎደል 6,5 ሚሊዮን መሆናቸው ነው)እ ጎ አ በ 2006 ዓ ም፤ የመስማት ችግር ያጋጠማቸው ወጣቶች፣ ከ ዚያ ፣ 12 ዓመት ቀደም ሲል ከነበረው ደረጃ 30 ከመቶ የጨመረ መሆኑን ትናንት ይፋ የተደረገ የጥናት ውጤት ጠቆመ። አብዛኞቹ ያጋጠመቸው እንከን ከባድ አይደለም ፤ ከልጃገረዶች ይልቅ፤ የሆነው ሆኖ፣ የላቀ ሳንክ ያጋጠማቸው ወንዶች ወጣቶች መሆናቸው ተደርሶበታል። Josef Shargorodsky የተባሉት ተመራማሪ ፣ በ 12 እና 19 ዓመት የዕድሜ እርክን መካከል በነበሩ በ 1771 ወጣቶች ላይ ሁለት ዓይነት መስማትን የሚመለከት ምርመራም ሆነ ፍተሻ አካሂደው ነበር። የመጀመሪያዎቹ ፍተሻዎች የተከናወኑት እ ጎ አ በ 1988 እና 1994 ዓ ም ሲሆን ያኔ 15 ከመቶ የሚሆኑት ወጣቶች የመስማት ችግር አጋጥሟቸው ነበር። በሁለተኛው ምርመራ በ 2005 እና በ2006 ዓ ም በተካሄደው ማለት ነው፤ ከ 19,5 ከመቶ ወደ 31 ከመቶ ከፍ ብሎ መገኘቱን ነው ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያ ያረጋገጡት።

መጠኑ እጅግ ከፍ ያለ ፣ለምሳሌ ያህል የመዚቃ መሳሪያ የሚያሰማው ድምጽ፤ የመስማት ደንቃራ ከሚፈጥሩት መካከል አንዱ መሆኑ አልታበለም። በአውስትሬሊያ በቅርቡ በልጆች ላይ የተካሄደ ጥናት እንደጠቆመውም ፣ የተጠቀሰው የሙዚቃ ጩኸት 70 ከመቶ ሳንክ እንደሚፈጥር ሳይደረስበት አልቀረም። መለስተኛ የመስማት ችግርም ቢሆን በንግግር ላይ እንከን ስለሚያስከትል ፤ በትምህርት ክትትል ላይ ጫና ያሳርፋል ጤናማ ስሜትንም ያዛባል ያሉት ተመራማሪ ቀላል የህክምና እርዳታ እንደሚበጅ ሳይጠቁሙ አላለፉም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ ፤ በወጣቶች ላይ የመስማት ሳንክ ያስከትላሉ በተባሉ ሰበቦች ዙሪያ ምርምር የማካሄዱ ተግባር መቀጠል እንደሚገባው ፤ ሻርጎሮድስኪ ሳይጠቁሙ አላለፉም።

በመጠኑ የሚባላ ቸኮሌት የልብ ድካምን ይከላከላል ተባለ፤

በእስዊድን ፤ 32,000 ገደማ የሚሆኑ ጠና ያሉ እስዊድናውያትን በማሳተፍ ረዘም ላለ ጊዜ የተካሄደ ጥናት እንደጠቆመው በተለይ ጠቆር ያለ ቸኮሌት በየዕለቱ ከ 19 እስከ 30 ግራም የሚመዝን አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ መብላት 32 ከመቶ የልብ ድካምን ይከላከላል። ውጤት የሚያስገኘው በቸኮሌት ውስጥ የሚገኘው የደም ግፊትን የሚያርቀው ፍላቮናይድ የተባለው ንጥረ ነገር ነው። በቦስተን፤ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ፤ የጥናቱ መሪ ሙሬይ ሚትልማን እንዳሉት፤ ቸኮሌት ለልብ ጠቀሜታ የሚኖረው፤ እንደተጠቀሰው፤ ተመጥኖ ሲወሰድ ብቻ ነው። በብዛት ከተባላ ግን የካሎሪው መጠን እጅግ ከፍ ስለሚልና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የክብደት መጨመር ስለሚያስከትል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል።

በርሊን የዓለም የሂሳብ መዲና ልትሆን ነው፤

ዓለም አቀፉ የሄሳብ ኅብረት (The International Mathematical Union)

ከመጪው 2011 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት አንስቶ፤ ቋሚ ማዕከል እንዲኖረው ሳይወስን እንዳልቀረ ፣ አንድ ዋና ጽ/ቤቱ በበርሊን የሚገኝ የምርምር ድርጅት አስታውቋል። በርሊን የተመረጠችው፤ ባንጋሎር ህንድ ውስጥ ተካሂዶ በነበረው ዓለም አቀፍ የሂሳብ ዐቢይ ጉባዔ ፣ከቶሮንቶ ፤ ካናዳ፤ እንዲሁም ከሪዮ ደ ጃኔሮ ፣ ብራዚል ጋር ተወዳድራ ነው። እስካሁን IMU በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር እንጂ ቋሚ በሆነ ጽ/ቤት አልነበረም ስብሰባ ሲያካሂድ የቆየው።

የታይላንድ አልጋ ወራሽ ልዕልት የጀርመንን ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ ጎበኙ፤ የታይላንድ አልጋ ወራሽ ልዕልት ማሃ ቻክሪ ሲሪንድሆርን፤ የሁለቱን አገሮች ሳይንሳዊ ትብብር ለማጠናከር በማሰብ ፤ ሃለ በተሰኘችው ከተማ የሚገኘውን ፣ ሊዮፖልዲና በመባል የታወቀውን ከፍተኛ የሳይንስ ምርምር ተቋም ጎብኝተዋል። የ 55 ዓመቷ አልጋ ወራሽ ልዕልት፤ የታይላንድ ንጉሥ የ ቡሚቦል አዱልያዴጅ ልጅ ናቸው። ሲሪንድሆርን ፤ በትምህርትና የጤና መርኀ-ግብር፤ በሰፊው የሚሳተፉ ሲሆን፤ የቀይ መስቀል ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት( ዩኔስኮ)፣ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ናቸው። ሊዮፖልዲና ፣ በሚል ስያሜ የታወቀው ሳይንሳዊ ምርምሮችን በማካሄድ የሰውን አኗኗርና የተፈጥሮ ይዞታን ለማሻሻል

ያለመው እ ጎ አ፤ ከ 2008 ዓ ም ወዲህ የጀርመን ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ የተባለው ከፍተኛ የምርምር ተቋም በመጀመሪያ የተመሠረተው እ ጎ አ በ 1652 ዓ ም ነው።

(ሙዚቃ)

ሃርቫርድ አሁንም ከዓለም ዩኒቨርስቲዎች የአንደኛነቱን ደረጃ እንደያዘ መሆኑ ተገለጠ። እ ጎ አ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ በያመቱ ፤ የዓለም ዩኒቨርስቲዎች የደረጃ ሠንጠረዥ የሚወጣ ሲሆን፤ በምሥራቅ ዩናይትድ እስቴትስ በማሳቹትስ ፌደራል ክፍለ-ሀገር የሚገኘው ሓርቫርድ ዩኒቨርስቲ አሁንም ለስምንተኛ ጊዜ የአንደኛነቱን ማዕረግ እንደያዘ ነው።

በአጠቃላይም የዩናይትድ እስቴትስ ዩኒቨርስቲዎች ሆነዋል የመሪነቱን ሥፍራ የያዙት፤ የዘንድሮው ሠንጠረዥ እንደሚያሳየው ከመጀመሪያዎቹ 10 ዩኒቨርስቲዎች 8ቱ ከዩናይትድ እስቴትስ ናቸው። ከመጀመሪያዎቹ አንድ መቶ ዩኒቨርስቲዎችም 54 ቱ ከዩናይትድ እስቴትስ ናቸው። ከሃርቫርድ ሌላ ከ 10 ውስጥ ካሊፎርኒያ፤ በርክሊ፤ እስንፈርድ፤ የማሳቹሰትስ የሥነ ቴክኒክ ተቋም፤ የካሊፎርኒያ የሥነ ቴክኒክ ተቋም፤ ፕሪንስተን ኮሎምቢያና ቺካጎ ይገኙበታል። ከ 2 ዓመት በፊት ከሃርቫርድ ቀጥሎ 2 ኛ የነበረው የል፤ ዘንድሮ 11 ኛ ለመሆን በቅቷል።የብሪታንያው ኬምብሪጅ አምና 4 ኛ ዘንድሮ ደግሞ 5ኛ ሆኗል። ኦክስፈርድ 10ኛ ነው። የተጠቀሰው ደረጃ የሚወጣው በአመዛኙ በሳይንስ የምርምር ወጤት በማስመዝገብ ነው። የእስያ-ሰላማዊው ውቅያኖስ አካባቢ አገሮች ዩኒቨርስቲዎች እመርታ በማሳየት ላይ ናቸው። ከብሪታንያ ዩኒቨርስቲዎች ሌላ ከፍተኛ ደረጃ ያገኘ ፤ በዙሪኽ የሚገኘው የአስዊዙ ፌደራል የሥነ ቴክኒክ ተቋም ነው። ደረጃው 24ኛ ነው። ከጀርመን ቀዳሚውን ቦታ የያዘው የሃይድልበርግ ዩኒቨርስቲ ሲሆን በዓለም ውስጥ ደረጃውም 57ኛ ነው። ከ 1-100 ባሉት አንድም ከላቲን አሜሪካና ከአፍሪቃ አይገኝበትም ፤ከመካከለኛው ምሥራቅ በኢየሩሳሌም የዕብራይስጥ ዩኒቨርስቲ 93 ኛ ደረጃ ላይ ሳይደርስ አልቀረም። በአፍሪቃ ፤ ከ 1-9 በሙሉ ከኬፕታውን ዩኚቨርስቲ ጀምሮ ሁሉም የደቡብ አፍሪቃ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ናቸው። 10Nq የካይሮ ዩኒቨርስቲ፤ 13ኛ የቀድሞው የአፍሪቃ ዝነኛ ዩኒቨርስቲ የዩጋንዳው ማካሬሬ ዩኒቨርስቲ ሆኗል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከአፍሪቃ የ 24ኛነቱን ደረጃ ይዟል።

(ዶ/ር ማሞ ሙጬ)----

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ