1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥቃት በኦታዋ ካናዳ ምክር ቤት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 13 2007

በካናዳዋ ኦታዋ ከተማ ምክር ቤት ትናንት ከደረሰዉ ድንገተኛ ጥቃት በኋላ የሀገሪቱ መንግሥት ለደህንነት እና የፀጥታ ጉዳይ ተቋማት ሰፋ ያለ መብትና ስልጣን ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1DbE6
Kanada Ottawa Anschlag Parlament Polizei 22.10.2014
ምስል Mike Carroccetto/Getty Images

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሀርፐር ለምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ የደህንነትና ፀጥታ ተቋማት የማሰርና የመፈተሽ ስልጣን እንዲሰጣቸዉ ታቅዷል። ትናንት በኦታዋ ምክር ቤት አቅራቢያ አንድ ወታደር ገድሎ ወደምክር ቤት የዘለቀዉ የ32ዓመት ጎልማሳ ምክር ቤቱ ዉስጥና በአቅራቢያዉ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ ያርከፈከፋቸዉ ጥይቶች ብዛት አጃቢ ያለዉ አስመስሎ ፖሊሶችን ቢያደናግርም ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚሉት ብቻዉን ነበር። የርሱም ህይወት አልፏል። ጥርጣሬዉን ማረጋገጥ የሚሻዉ ፖሊስ ግን ክትትሉን እንዳላቆመ ገልጿል። ከሞላ ጎደል በተረጋጋ ፀጥታዋ በምትታወቀዉ ካናዳ የደረሰዉ ጥቃት ዜጎችን ብቻ ሳይሆን መንግሥትንም ያደናገጠ ብሎም ያባነነ መሆኑ እየተገለጸ ነዉ። ስለሁኔታዉ የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ