1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥንታዊ የድንጋይ ቅርጽና ተፈጥሮዋዊ ሃብት በጌዶ ዞን

ዓርብ፣ ኅዳር 13 2000

የሰዉ ዘር መገኛ ድንቅ ባህል እና የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ኢትዮጽያ በጉያዋ ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩባት ስትሆን በስተ-ደቡብ ኢትዮጽያ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ዋና ከተማ ከሆነችዉ አዋሳ በስተ-ደቡብ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ የጌዶ ዞን ዋና ከተማዉን ዲላ አድርጎዋል። በዚሁ ዞን እስካሁን በተደረገዉ ጥናት በግምት 1.2 ሚሊዮን ህዝብ እንደሚገኝም የአካባቢዉ ባለሞያዎች ይገልጻሉ

https://p.dw.com/p/E0lz
ምስል AP
የጌዶ ዞን መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ የተለያየ የአየር ጸባይ ቢታይም በአብዛኛዉ የወይና ደጋማ እንደሆነ ጹሁፎች ያሳያሉ። ከአዲስ አበባ 395 ኪሎሜትር ርቃ የምትገኘዋ ይርጋ ጨፊ ከተማ እና አካባቢዋ አለምን በአስደመመዉ የቡና እና የእንሰት ምርት ታዋቂ አድርጓታል። ጌዶ ዞን ተፈጥሮ ከለገሰዉ የተለያየ አዝርት እና እፀዋት ሌላ ከድንጋይ የተፈለፈለ የሰዉ አካል ቅርጽን የያዘ ጥንታዉ የተክል ድንጋይ ቅርጻ ቅርጽም ይገኛል። የአካባቢዉ ተጠሪዎች ይህንን የተለየያየ የእጽዋት ሃብት እና ጥንታዊ ቅርጻ ቅርጽ ሃብት፣ በአለም ቅርጽነት እንዲመዘገብ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።። በቅርቡ በተካሄደዉ የባህላዊዉ ምግብ ዉድድር የጌዶ ዞን ከቆጮ የተሰሩ የተለያዩ ምግቦችን በማቅረብ አንደኛነትን አግኝቷል።