1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፀረ ኤቦላ ትግሉን የማስተባበሩ ጥረት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 2007

በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሲየራ ልዮን የብዙ ሺዎችን ሕይወት እያጠፋ ያለውን የኤቦላ ወረርሽኝ ለማጥፋት ከያቅጣጫው ጥረቱ ተጠናክሮዋል። በዚሁ መሠረትም፣ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች ባለፈው ዓርብ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን የፀረ ኤቦላ ትግል ግብረ ኃይል አስተባባሪ በጠራው ስብሰባ ላይ በመገኘት

https://p.dw.com/p/1E5YW
Ebola DRK Liberia
ምስል DRK/Victor Lacken

የተጠቂዎቹን ልዩ ሁኔታ በመገምገም አስፈላጊውን ርዳታ በተቀናጀ መንገድ ማቅረብ ስለሚቻልበት ጉዳይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። የኤቦላ ወረርሽኝ ያስከተለውን እና ሊያስከትል የሚችለውን የጤና፣ ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ የሚገመግም አንድ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በሚቀጥለው አዲሱ አውሮጳዊ ዓመት 2015 ሊጠራ ስለሚችልበትም ጉዳይ የስብብሰባው ተሳታፊዎች መክረዋል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ በወረርሽኙ አንፃር ስለተጀመረው ትግል በዩኤስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የኤቦላ አስተባባሪን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ