1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፀረ የባህር ላይ ውንብድና ተልዕኮ ስኬት

ዓርብ፣ መጋቢት 13 2005

ከአውሮፓ ጋር ከሚደረገውዓለም ዓቀፍ ንግድ 80 በመቶው በአደንባህረሠላጤበኩልየሚያልፍነው። በአካባቢው የባህር ላይ ውንብድናን ለመከላከል የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ባህር ኃይል ከተሰማራበት ከ ዛሬ 5 አመት ወዲህ ዘረፋና እገታው በእጅጉ ቀንሷል።

https://p.dw.com/p/182qO
ምስል picture-alliance/dpa

በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ የባህር ላይ ውንብድና የሚፈፀምባቸው ዋነኛዎቹ አካባቢዎች ምዕራብ አፍሪቃን የሚያዋስነው የውሐ ክልል ፣ በኢንዶኔዥያ ዙሪያ የሚገኙ ባህሮችና የሶማሊያ የባህር ዳርቻ አካባቢዎች ናቸው ። በተለይ በሶማሊያው ጠረፍ የሚካሄደው የባህር ላይ ውንብድና እስካሁን ወደር አልተገኘለትም ። ከአውሮፓጋርከሚደረገውዓለም ዓቀፍ ንግድ 80 በመቶው በአደንባህረሠላጤበኩልየሚያልፍነው። በአካባቢው የባህር ላይ ውንብድናን ለመከላከል የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ባህር ኃይል ከተሰማራበት ከ ዛሬ 5 አመት ወዲህ ዘረፋና እገታው በእጅጉ ቀንሷል ። ከ5 አመታት ወዲህ ተባብሶ በነበረው የባህር ላይ ውንብድና ምን ያህል የሰው ህይወት እንደጠፋ እስካሁን በውል አልታወቀም ።

Piraterie Bildergalerie
ምስል Anonymous/AP/dapd

በርሊን የሚገኘው የምጣኔ ሃብት ምርምር ተቋም ከባህር የሚዘረፈውና የተጋቱ ሰዎችን ለማስለቀቅ የሚሰጠውን ገንዘብ በአመት ከ 7 እስከ 12 ቢሊዮን ዮሮ እንደሚደርስ አስልቷል ። ከባህር ላይ ውንብድና ለመሸሽ የባህሩን መንገድ መቀየር መፍትሄ አይሆንም ። መርከቦች ስዌዝ ካናልን ትተው በ17 ተኛው ክፍለ ዘመን እንደሚደረገው መላ አፍሪቃን ቢዞሩ ጉዞው በ 2 ወራት ሊዘገይ ከመቻሉም በላይ ተጨማሪ 30 ቢሊዮን ዩሮ ያስወጣል ። ዓለም ዓቀፍ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት እጎአ ከ 2005 እስከ 2008 ስለተካሄደው የባህር ላይ ውንብድና ባቀረበው ዘገባ በመቶዎች ይቆጠር የነበረው የዘራፊዎች ቁጥር ከ አንድ ሺህ በላይ ማደጉን አስታውቋል ። በ 2005 ፣300 ያህል ጥቃት መድረሱንም አስታውሷል ። እጎአ ከ 2008 ወዲህ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰቡ የባህር ኃይል ዝርፊያና እገታ ይካሄድባቸው በነበሩ አካባቢዎች ሰፍሯል ።

አታላንታ በተሰኘው የአውሮፓ ህብረት ተልዕኮ ሥር የዘመቱት የጀርመን ባህር ኃይል መርከቦችም የንግድ መርከቦችን ከጥቃት እየጠበቁ ነው ። ከዚያን ጊዜ አንስቶም የሚጠለፉና የሚጠቁ መርከቦች ቁጥር ቀንሷል ። እጎአ በ 2010 ፣ 47 የነበረው የታገቱ መርከቦች ቁጥር በ 2011 25 በ 2012 ደግሞ 5 ብቻ ነው ። ለንደን የሚገኘው የዓለም አቀፍ የባህር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ፖቴንጋል ሙኩንዳን ይህ ሊሳካ የቻለው በዓለምዓቀፉ ባህር ኃይል ጥረት መሆኑን ያስረዳሉ ።

Piraterie Bildergalerie
ምስል picture-alliance/dpa

«ዋናው ጉዳይ የባህር ኃይሎቹ ተጠርጣሪ እናት መርከቦች ፣ የንግድ መርከቦችን ማጥቃት የሚችሉበት ደረጃ ላይ ሳይደርሱ በመከታተል የተጫወቱት ወሳኝ ሚና ነው ። ሁለተኛው ምክንያት በመርከቦች ውስጥ የግል ታጣቂ የፀጥታ አስከባሪዎች ቁጥር መጨመር እንዲሁም ሶስተኛው ምክንያት መርከቦቹ የባህር ላይ ወንበዴዎች ወደ መርከቦቹ እንዳይገቡ ለመከላከል የሚወስዷቸው እርምጃዎች ናቸው ። »

በነዚህ እርምጃዎች ምክንያት በአደን ባህረ ሰላጤየባህርላይውንብድና መመናመኑን የተናገሩት ሙኩንዳ ዘረፋው ከጥቂት ወራት ወዲህ ወደሌላው አካባቢ ተሸጋግሯል ይላሉ ።

Piraterie Bildergalerie
ምስል picture-alliance/dpa

«ባለፉት 12 ወራት ጥቃቱ ወደ ቶጎ ና ቤኒን የውሐ ክልል ተሻግሯል ። በቅርቡም በአይቮሪኮስት የባህር ክልል 3 ነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ደርሷል ። የዚህ ጥቃት አላማም መርከበኛውን ማገትና ምናልባም ከ 3 እስከ 4 ሺህ ቶን የሚደርስ ነዳጅ ዘይት መስረቅ ነው »

የጀርመን ባህር ኃይል ተልዕኮ መራዘም ችግሩን ለማቃለል ብዙ አስተዋፅኦ አድርጓል ። ለዚህም ባለፈው አመት ወደ ጅቡቲ በመሄድ የባህር ኃይሉን እንቅስቃሴ የተመለከቱት ፎርስተር ሽታፌልድስ የጀርመን ነፃ ዲሞክራቶች ፓርቲና የህዝብ እንደራሲዎች ምክር ቤት አባል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ።

« የጀርመን ባህር ኃይል እዚያ የሚቆይበት ጊዜ ባለፈው አመት በግንቦት መራዘሙ ማለትም ከጠረፍ 2 ሺህ ሜትር ርቀት ድረስ እንዲቆጣጠር መደረጉ የባህር ላይ ወንበዴዎቹ ከባህር ወደ ጠረፍ ለመመለስ አዳጋች ሆኖባቸዋል ። ይሄ አንድ ጠቃሚ ነጥብ ነው ። ከዛ በፊት ግን ጀልባዎቻቸው ወደ ጠረፍ እየተመላለሱ ቤንዚንም ጦር መሣሪያም እየጫኑ ይሰማሩ ነበር ። አሁን ግን ያሁሉ ተሰናክሎባቸዋል ። »

ቮልፍጋንግ ዲክ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ