1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይና ስደተኖች

ሐሙስ፣ ነሐሴ 28 2007

በስደተኞች ቀባበልና ለሚቀርብላት የተገን ጥያቄ ማመልከቻ አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠት የምትወቀሰዉ ፈረንሳይ ሰሞኑን በስደተኞች ላይ የሚደርሰዉን አስከፊ ቀዉስ በተመለከተ የተለየ አቋም ይዛ ታይታለች።

https://p.dw.com/p/1GQgL
Frankreich Manuel Valls in Calais mit Timmermans und Avramopoulos NEU
ምስል Getty Images/AFP/D. Charlet

[No title]

ሰኞ ዕለት ከአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ተወካዮች ጋር በመሆን ወደፈረንሳይዋ የወደብ ከተማ ካሌ ያቀኑበት የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ቫልስ እዚያ የሚገኙ ስደተኞችን ሁኔታ ከተመለከቱ በኋላ 1,500 ስደተኞችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ የስደተኞች መቀበያ ማዕከል ካሌ ላይ ሀገራቸዉ እንደምትከፍት አስታዉቀዋል። ስደተኞችም እንደሰዉ ሊከበሩና ሰብዓዊ መብታቸዉ ሊጠበቅ ይገባልም ማለታቸዉ ተሰምቷል። ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ዕቅድ በሌሎቹ የፈረንሳይ ፖለቲከኞች እና ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ተቋማት ተተችቷል። ወደእንግሊዝ ለመሻገር የሚመኙ ስደተኞች ወደሚከማቹባት የወደብ ከተማ ካሌ ደርሳ የተመለሰችዉ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ