1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ፊደል» የትምህርት ድረ ገፅ

ዓርብ፣ ግንቦት 1 2006

ሁለት በጀርመን የሚኖሩ ወጣቶች በተለይ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆን አንድ የትምህርት መማሪያ ድረ ገፅ ሰርተዋል።ስለዚህ የትምህርት ድረ ገፅ አላማ እና አጠቃቀም መስራቾቹ በዛሬው የወጣቶች ዓለም ይገልፁልናል።

https://p.dw.com/p/1BvuA
Plattform Fidel
ምስል Ahadoo Tec

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መጠቀም የሚቻለው ይኼው «ፊደል» የተሰኘ ድረ ገፅ፤ ተማሪዎች በተለይም የሂሳብ እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ይረዳል። መስራቾቹ እስክንድር ተስፋዬ እና አማኑኤል አማረ ይባላሉ።እስክንድር የንግድ አስተዳደር አማኑኤል ደግሞ የሶፍት ዌር ባለሙያ ናቸው። ሁለቱም «አህዱ ቴክ» የተሰኘ ኩባንያ መስርተዋል። ኩባንያውም ስራውንም ከየካቲት ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ጀምሯል። የዚህም ስራ ውጤት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ለተማሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል ዘመናዊው የትምህርት ድረገፅ ነው።ፊደል መቼ እና እንዴት ተጀመረ? መስራቾቹ ያስረዳሉ።

የጥናት ፍላጎትን ከጨዋታ ጋር በማዛመድ እንዲሁም ከሌሎች የ«ፊደል» ተጠቃሚዎች ጋር በመፎካከር ለበለጠ ውጤት ተማሪዎች ሊበረታቱ እንደሚችሉ መስራቾቹ ይገልፃሉ። የፊደል ድረ ገፅ ላይ የሚመዘገቡ ወጣቶች በአሁን ሰዓት ማጥናት የሚችሉት የሂሳብ ትምህርትን ነው። እንደ አልጄብራ፣ሎጋሪዝም የመሳሰሉ የሂሳብ ትምህርት ጥያቄዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ድረ ገጹ ላይ ይገኛሉ። ወደፊትም «ፊደል» ሌሎችንም የትምህርት አይነቶች ያካተተ መድረክ ለተጠቃሚዎቹ የማቅረብ ዓላማ አለው። ይህም ከተለያዩ ተቋሟት እና ድርጅቶች ጋር በጋራ በመስራት ነው።

Plattform Fidel
አማኑኤል አማረ (በስተ ግራ)እስክንድር ተስፋዬ ( መሀከል)ምስል Ahadoo Tec

«ፊደል» የተሰኘ የትምህርት ድረ ገፅ ለተማሪዎች ካቀረቡት «የአህዱ ቴክ ኩባንያ» መስራቾች እስክንድር ተስፋዬ እና አማኑኤል አማረ ጋር በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ