1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፍንዳታ በሞስኮ ምድር ባቡር

ማክሰኞ፣ መጋቢት 21 2002

ትናንት ጠዋት ከምድር በታች በሚገኙ የባቡር ጣቢያዎች በደረሱ ሁለት የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታዎች 39 ሰዎች በተገደሉባት በሩስያ ዛሬ የሀዘን ቀን ታውጇል ።

https://p.dw.com/p/MhlB
ምስል AP
በርካቶችም የቆሰሉበትን ይህን አደጋ ያደረሱት ሁለት ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች መሆናቸውን የሞስኮ ከንቲባ ዩሪ ሉትሽኮቭ ገልጸዋል። እስካሁን ለአደጋው ሀለፊነቱን የወሰደ ወገን ባይኖርም የሩስያ የደህንነት መስሪያ ቤት ግን ለሁለቱ አደጋዎች ተጠያቂዎቹ ቼችንያን የሚያጠቃልለው የካውካሱስ ግዛት አማፅያን ናቸው ተብሎ እንደሚታመን ተገልጾአል። ዝርዝሩን ገበያዉ ንጉሴ ከብራስልስ ልኮልናል ገበያዉ ንጉሴ፣ አዜብ ታደሰ ሂሩት መለሰ