1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፔተር ሊምቡርግ የወደፊቱ የዶይቸቬለ አስተዳዳሪ

እሑድ፣ መጋቢት 8 2005

ፔተር ሊምቡርግ የወደፊቱ የዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ዛሬ ተመረጡ ። የዶይቸ ቬለ የመገናኛ ብዙሃን ስርጭት ቦርድ ሊቀመንበር ቫለንቲን ሽሚት ሊምቡርግ መመረጣቸውን በርሊን ውስጥ ከተካሄደ ስብሰባ በኋላ አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/17ylm
Peter Limbourg, derzeitiger Informationsdirektor von ProSiebenSat.1 TV Deutschland, wird neuer Intendant der Deutschen Welle und Nachfolger von Erik Bettermann, dessen Amtszeit am 30. September endet.
ምስል picture-alliance/dpa
Deutsche Welle Bonn Funkhaus Gebäude Schürmann Bau Foto DW/Per Henriksen 04.09.2012. # DW2_6035.
የዶይቸ ቬለ የቦን መቀመጫምስል DW

የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያ ፣ የፕሮዚብን ዛት አይንስ የኢንፎርሜሽን ክፍል ሃላፊ ሊምቡርግ ፣ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ በአብላጫ ድምፅ ነው የተመረጡት ። ከ17ቱ የቦርዱ አባላት 14 ቱ የድጋፍ ድምፅ ሲሰጧቸው አንድ የተቃውሞ ና 2 ድምፀ ተዐቅቦም ነበር ።
ፔተር ሊምቡርግ ፣ እ ጎ አ መስከረም 30 2013 የሥልጣን ዘመናቸው የሚያከትመውን የ68 አመቱን ኤሪክ ቤተርማንን ተክተው ያገለግላሉ ። ቤተርማን፤ እ ጎ አ ከ 2001 ዓ ም አንስቶ ዶይቸ ቬለን ያስተዳደሩና ፤ ድርጅቱ አዳዲስ አገልግሎቶችን እንዲያቀርብ በመቀየስ ጭምር የሚታወሱ ስራ አስኪያጅ ናቸው ።
« ዶይቸ ቬለ የጀመረውን አዳዲስ አገልግሎቶች የበለጠ አጠናክሮ የጀርመንን የአለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረት እንዲያሻሽል ፔተር ሊምቡርግ የሚጠበቅባቸውን በሙሉ የሚያሟሉ ጋዜጠኛ ናቸው» ሲሉ፤ ሽሚት ተናግረዋል።

በተለያዩ ቋንቋዎች የዶቼቬለን የመገናና ብዙሃን አገልግሎት ማስፋፋት

የ 52 አመቱ ሊምቡርግ የዶቹቬለ የመገናኛ ብዙሃን ስርጭት ቦርድ በርሳቸው ላይ ፅኑ እምነት በመጣሉ አመስግነዋል ። « በሚመጡት አመታት አገራችን በአለም ውስጥ ያላትን ተቀባይነት ለማጎልበት ካለው ተግዳሮት አንፃር ባለኝ አቅም ሁሉ የሚቻለኝን አደርጋለሁ ። ከወጣትነቴ አንስቶ ከጀርመን ውጭ ባሳለፍኳቸው ጊዜያት የዶይቸ ቬለ ዝግጅቶች ጠቃሚ የህይወት ተሞክሮዮ አካል ነበሩ ። ከባልደረቦቼ ጋር የዶቼቬለን የጋዜጠኝነት በጎ ስም በመጠበቅ ፣ የራድዮ ጣቢያውን የተለያዩ ቋንቋዎችና የተለያዩ የመገናና ብዙሃን አገልግሎቶች ይበልጥ ማዳበር እፈልጋለሁ። ሌላው ግቤ ዶቼቬለ እንደ ARD እና ZDF ካሉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ከሚሰጡ ከሌሎች የጀርመን ጣቢያዎች ጋ ትብብሩን ይበልጥ ማጠናከር ነው ። »
ፔተር ሊምቡርግ የብሔራዊ ወታደራዊ አገልግሎት ካጠናቀቁ በኋላ በቦን ከተማ የህግ ትምህርት አጥንተዋል ። እ ጎ አ 1987 ዓ ም የመጀመሪያውን የህግ ብሔራዊ ፈተና ወሰዱ። ከዚያም እጎአ ከ1988 እስከ 1989 በጀርመን የቴሌቪዥን ጣቢያ (DFA) በቦን እና በለንደን ከተማ የጋዜጠኝነት ስልጠና ወስደዋል ።
በቀድሞዋ የምስራቅ ጀርመን ከተማ ላይፕዚግ በዘጋቢነት የሰሩት ሊምቡርግ እጎአ ከ1990 ጀምሮ የአውሮፓ እና የኔቶ ቃል አቀባይ በመሆን ለጀርመን ዲ-ኤፍ-ኤ እና ዛት-አይንስ ጣቢያዎች ከብራስልስ ይዘግቡም ነበር ። እጎአ በ1996 የፕሮዚብን ጣቢያን ሃላፊነት ተረከቡ ። በ 1999 የ N24 ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና አዘጋጅነት እና በፕሮዚብን ጣቢያ የፖለቲካ ክፍል ኃላፊነት ማገልገል ጀመሩ። እጎአ 2004/05 እና 2008/09 ከበርሊን በሚሰራጨው ፑል-በተባለው የግል ቴሌቬዥን ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅነት ፣ ከ2008-2010 ደግሞ ተመልሰው በ N24 ጣቢያ በዋና አዘጋጅነት አገልግለዋል ። ከ 2008 አም አንስቶ የዛት አይንስ ቴሌቪዥን ዜና አቅራቢ፣ ከ2010 ዓም አንስቶ ደግሞ የፕሮ ዚብን ዛት አይንስ ነባር ምክትል ፕሬዝዳንትም ነበሩ ። ሊምቡርግ የጀርመን ፌደራላዊ ምክር ቤት የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት ዳኞች ሊቀመንበር፣ አክስል ሽፕሪንገር አሳታሚ ድርጅት -ለወጣት ጋዜጠኞች የሚሰጠው ሽልማት ዳኞች ቡድን አባል፣ የጀርመን የጳጳሳት ጉባዔ አሳታሚ ኮሚሽን አማካሪ እና የካቶሊካዊያን የግብረ ሰናይ ድርጅት የ« ማልቴዘር »አባልም በመሆን አገልግለዋል። ቦን ከተማ የተወለዱት ሊምቡርግ ፣ ያደጉት ሮም ፣ፓሪስ አቴንስና ብራስልስ ነው ። ሊምቡርግ ባለትዳር እና የ ሶስት ልጆች አባት ናቸው።

Erik Bettermann, Intendant der Deutschen Welle
ኤሪክ ቤተርማን ለ12 አመታት በዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል።ምስል DW

ዮሀንስ ሆፍማን

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Bald Führungswechsel bei der DW