ፔን እስክንድር ነጋን ሸለመ
ዓርብ፣ ጥቅምት 12 2008ማስታወቂያ
መቀመጫውን በቶሮንቶ ካናዳ ያደረገው ፔን ካናዳ የተባለ ለፍትና ጋዜጠኞች መብት የሚሟገት ድርጅት በኢትዮጵያ በእስር ላይ ለሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ «one humanity award» የተባለውን ሽልማት እንደሚያበረክት ገለጸ። ሽልማቱም የ5 ሺ ዶላር ዋጋ አለው ተብሏል። ፔን ካናዳ ከ 148ቱ የፔን ዓለም አቀፍ ማዕከላት መካከል አንዱ ሲሆን ሽልማቱን በየዓመቱ የሚያበረክተው በጽሁፎቻቸው በሚያነሷችው ሀሳቦች ድንበር ሳያግዳቸው በተለያየ ባህል እና ወግ ውስጥ የሚኖረውን ኅብረተሰብ ማስተሳሰር ለቻሉ ፀሀፍት አልያም ጋዜጠኞች ነው። በጎርጎሮሳዊው ከታህሳስ 22 እስከ ህዳር 1 ቀን 2015 በሚቆየው 36ኛው ዓለም አቀፍ የፀሀፍት ፌስቲቫል ላይ ነው «ፔን ካናዳ» ሽልማቱን ለታሳሪው ጋዜጠኛ የሚያበረክተው። የፔን ኢትዮጵያ ተወካዮች እስክንድርን በመወከል ሽልማቱን ይቀበላሉም ተብሏል። ናትናኤል ወልዴ ከዋሽንግተን ዲሲ ተጨማሪ ዘገባ ለኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
አዜብ ታደሰ