1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሪዝደንት ፑቲን በቴህራን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 5 2000

የሩስያዉ ፕሪዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የካስፒያን ባህር ጉባኤ ተገኙ። ባለፉት ቀናት በቴህራን ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ይደረጋል የሚል ዘገባ ተናፍሶ፣ ፑቲን ይህ ወሪ እንደማያስበረግጋቸዉ ነበር በማስረገጥ የገለጹት። ይህ ዛሪ ከተጠናቀቀዉ ጉባኤ ሌላ በምዕራባዉያን እና በኢራን መካከል በመሻከር ላይ ያለዉን ግንኙነት ለቴህራን መንግስት እንደሚያሳዉቁም ይጠበቃል። ቴህራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዳይጣል ፑቲን በቴህራን ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/E87f
በቴህራን የአቀባበል ስነ-ስርአት ላይ
በቴህራን የአቀባበል ስነ-ስርአት ላይምስል AP

የሩስያዉ ፕሪዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት በጀርመን የቪዝባድኑን ተልኮአቸዉን ጨርሰዉ ወደ ቴህራን የሚጓዙበት ሰአት በዉል አልታወቀም ነበር። የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች የሩስያዉ ፕሪዝደንት አመሻሹ ላይ ቴህራን እንደሚደርሱ አልያም ከጀርመን እንደሚነሱ ነበር የዘገቡት። በሩስያ የሚገኙት አንዳንድ የመገኛኛ ብዙሃን ደግሞ በቴህራን አንደ አጥፍቶ ጠፊ በፕሪዝደንቱ ላይ የግድያ ሙከራ እንደሚጣል ስለተዛተ ፕሪዝደንቱ ጉዞአቸዉን ሰርዘዋል ሲሉ ነበር ዘገቦቻቸዉን ያሰሙት። ፑቲን በጉዳዩ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ ምልልስ የግድያ ዛቻ ቢጣልም (በርግጥ ወደ ቴህራን መጓዜ አይቀርም) ሲሉ ነበር በማስረገጥ የገለጹት። (በአንዳንድ ጋዜጦች ወይም በተባራሪ ወሪዎች የሚበረገግ ቢሆንማ ባጠቃላይ ከቤት መዉጣት አያስፈልግም ነበር። እዝያዉ እቤት መቀመጥ ይሻላል) በአገራቸዉ በሩስያ ማለታቸዉ ነበር። እ.አ በ1979 በኢራን የተጀመረዉ እስላማዊ አብዮት በመባል የሚታወቀዉ የኢራን አብዮት በአገሪቷ ብቅ ካለ ወዲህ የክሪምሊን መንግስት ወደ ኢራቅ ሲጓዝ ፑቲን የመጀመርያዉ ፕሪዝደንት ናቸዉ።

እ.አ 1943 አ.ም የሶቭየት ህብረት አንባገነን በመባል የሚታወቀዉ ዮሴፍ ስታሊን ኢራንን የጎበኘ የመጨረሻዉ የሶቭየት ህብረት ባለስልጣን እንደነበር ጹሁፎች ያስረዳሉ። የፑቲን ኢራንን ጉብኝት ሩስያ የኢራን የኒኩልየር ሃይል መረሃግብሯን እንድታጠናክር ድጋፍ ይሆናል፣ ምዕራባዉያን በኢራን ሊያጠናክሩት ያቀዱት የእቀባ እቅድም ይረግባል የሚል ተስፋ በቴህራን መንግስት ይታያል። ፕሪዝደን ፑቲን ቴህራን እንደደረሱ የኢራን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር Manuchehr Mottaki አቀባበል ሲያደርጉላቸዉ የኢራን የመንግስት ቴሌቭዥን አሳይቷል። በካስፒያን ባህር ጉባኤ ላይ ከሩስያ እና ከኢራን ቀጥሎ የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ግዛት የነበሩት የካዛኪስታን የቱርክሜኒስታን እና የአዘርባጃን መንግስታት ተሳታፊ ናቸዉ። ፑቲን በካስፒያን ባህር ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸዉ የካስፒያን ባህር የሚያዋስኑትን አምስቱን አገሮች ለጋራ ጥቅም የትብብር ስራ እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።
ፑቲን በጉባኤዉ ላይ በመቀጠል
(ለኛ አገር በህይወት መቆየት የካስፕያን ባህር ትልቅ ሚናን ይጫወታል። ዛሪ በዚህ በካስፒያን ባህር ጉባኤ አምስት የተለያየን መንግስታት ብንሰበሰብም፣ ባህሩ ለሁላችንም አንድ ሆኖ ይቆየናል። ይህን ባህር ለ5 ባህሮች ብንከፋፍለዉ ኖሮ ምንኛ ትልቅ ስህተት በሆነ ነበር። ታድያ ጥቅም ለማግኘት መልሱ፣ ከርሰ ምድር ዉስጥ የሚገኘዉን፣ ተከፋፍለን፣ ባህሩ ግን፣ ለሁላችንም በአንድነት ለጋራ ጥቅም እናዉለዋለን። ይህ ታድያ የሁላችንም ፍላጎት ይመስለናል)

አህመዲን ነጃድ በበኩላቸዉ የጉባኤዉን ተካፋይ አገሮች ለሰላም ጥረት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። አምስቱ አገሮች ትብብር ይላሉ አህመዲን ነጃድ ለአካባቢዉ ሰላም ብቻ ሳይሆን ለአለም ሰላምም ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል። ጉባኤዉ በካስፓን ባህር ከርሰ ምድር የሚገኘዉን ከፍተኛ የጋዝ የነዳጅ ዘይት ጥርቅም እንዴት መጠቀም እንችላለን በሚል ሲሆን አምስቱ አገሮች የመጀመርያ ጉባኤያቸዉን እ.አ 2002 አ.ም በከርሰ ምድሩ የሚገኘዉን ጥሪ ሃብት አጠቃቀም ላይ ሳይስማሙ መበተናቸዉ ይታወሳል።
ይህ ዛሪ የተደመደመዉ የካስፓን ባህር ጉባኤ መጠናቀቅያ ላይ የኢራኑ ፕሪዝደንት በመዝግያ ንግግራቸዉ ጉባኤዉ በጥሩ የጓደኝነት ስሜት ተካሆዶአል፣ አምስቱ አገሮች ታሪካዊ የሆነ የትብብር ስራ ለመስራት መነሳታቸዉ አዲስ ምዕራፍ ነዉ፣ ትልቅ ዉጤት ሲሉ ገልጸዋል። የሩስያዉ ፕሪዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በቪዝባደን የኢራን አተም መረሃ ግብር በተመለከተ ከኢራን መንግስት ዉይይት እንዲ ጀመር ሊጣል የታሰበዉም ማዕቀብ ትንሽ እንዲጤንበት ማሳሰባቸዉ ይታወሳል። ፑቲን በኢራን ጉብኝታቸዉ ከቴህራን መንግስት ጋር ሌላዉ የመወያያ ርዕሳቸዉ እንደሆን ይጠበቃል።