1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚዳንት ዙማ ስልጣን እንዲለቁ የተጠራ ከፍተኛ ተቃዉሞ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 5 2009

በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ሰባት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የጠሩት የተቃዉሞ ሰልፍ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠየቁ። ተቃዋሚዎቹ ባወጡት መግለጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተለያዩ አቋሞችን የሚያራምዱ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ የሚከተሉት መንገድ ሃገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ትርምስ ከማምራቱ በፊት ስልጣን ይልቀቁ ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2bD96
Südafrika Proteste gegen Präsident Zuma
ምስል Reuters/M. Hutchings

 

በ 10 ሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎች የታጀበዉ የተቃዉሞ ሰልፍ የተካሄደዉ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ፤ ትናንት 75ኛ የልደት በዓላቸዉን በሚያከብሩበት እለት ነዉ። የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ «ANC» ደጋፊዎች ለፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ 75 ኛ የልደት በዓል ሽር ጉዳድ ሲሉ ተቃዋሚዎች የሲቢክ ማኅበራትና ደጋፊዎቻቸዉ መነሻዉን የመንግሥቱ መቀመጫ ከሆነዉ ፕሪቶርያ ቸርች ስኩየር አደባባይ በመሰባሰብ ተቃዉሞአቸዉን አሰምተዋል።

መላኩ አየለ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ