1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

(1)በአርክቲክና በአንታርክቲካ የበረዶ መቅለጥ ያሳዳረው ሥጋት፣ (2)የሰረንጌቲ ባለውለታ፣

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 22 2001

በአንታርክቲካ፣ መጠኑ፣ የኒው ዮርክን ከተማ ያህል ስፋት ያለው የረጋ የበረዶ ኮረብታ፣ በዚህ ወር ውስጥ፣ በምድራችን የሙቀት መጠን መጨመር ሳቢያ፣

https://p.dw.com/p/Hgwq
በአርክቲክና በአንታርክቲካ የበረዶ መቅለጥ ያሳዳረው ሥጋት፣
የታንዛንያው የሰረንጌቲ መንበረ- ዐራዊት፣ እንዲጠበቅ ዐቢያ አስተዋጽዖ ያደረጉት፣ የበርንሃርት ዥሜክና የልጃቸው ሚሻኤል ዥሜክ መቃብር፣ በዚያው የዱር ዐራዊትና እንስሳት ክልል፣ምስል AP

የመፈረካከስ አደጋ እንደተደቀነበት፣ ተነገረ። በሰሜናዊው አንታርክቲካ፣ «የዊልክንስ የበረዶ ንጣፍ በመባል የታወቀው በረዶ የሸፈነው ቦታ፣ባለበት መርጋት አለመቻሉንና መፈርከሱን ያስረዱት፣ በጀርመን የሙዑንስተር ዩኒቨርስቲ የበረዶ ይዞታዎች ተመራማሪ ወ/ሮ አንጌሊካ ሁምበርት ናቸው። ሁምበርት እንዳሉት በአንታርክቲካ ከውቅያኖስ ጋር ፣ ድንበር የሚፈጥር አዲስ የረጋ በረዶ ወሰን እስኪሠት ድርስ፣ አሁን ሰሚናዊው ጫፍ ላይ ያለው፤ ከ 570- 3,370 እስኩየር ኪሎሜትር የሚገመት፣ የበረዶ ጉብታ፣ በሚመጡት ቀናት ተፈርክሶ ውቅያኖስ ላይ መንሳፈፉ አይቀሬ ነው።

ተመራማሪዋ፣ ይህን ያሉት፣ የአውሮፓው የኅዋ ድርጅት ሳቴላይት ያነሳቸውን ፎቶግራፎች ከመረመሩ በኋላ ነው። የ «ዊልክንስ » የበረዶ ንጣፍ 16,000 እስኩየር ኪሎሜትር ያህል ስፋት የነበረው ሲሆን እ ጎ አ፣ በ 1990ኛዎቹ ዓመታት መሸርሸር ጀምሮ አሁን ከደረስንበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

ተክሌ የኋላ፣