1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሰመራ

ዓርብ፣ ኅዳር 29 2010

12ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ዛሬ ተከበረ። ይህ በዓል ዘንድሮ የተከበረዉ በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2p2IV
Äthiopiens - Afar Region: Tag der Nationalitäten
ምስል DW/Y. Gebireegziabher

የዘንድሮዉ በአፋር ክልል ሰመራ ተከበረ፤

 በበዓሉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፤ የሀገሪቱ የፌደራል ሥርዓት የሕዝቦችን እኩልነት ያመጣ እና ህዝቡንም የልማት ተጠቃሚ ያደረገ ነዉ ማለታቸዉን በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። ከዚህም ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠንካራ አለት ላይ የተመሠረተች ታላቅ እና የበለፀገች ሀገር ለማነፅ በርትተን እየሠራን ነዉ ማለታቸዉንም አመልክቷል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ