1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

121ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል

ዓርብ፣ የካቲት 24 2009

«አድዋ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው የጥቁር ሕዝብ የድል በዓል ነው።  የዓለም ጥቁሮች ሲያከብሩት እኛ ልንኮራበት እንጂ ልንወዛገብበት አይገባም።  እንኳን ለአድዋ ድል በዓል አደረሰን። ለበዓሉ መታሰቢያ ከአያቴ ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ግጥሞች አንዱን ልኬያለሁ »

https://p.dw.com/p/2YYYH
Äthiopien Addis Abeba Annual national celebrations Adwa Victoy
ምስል Abel Wabella

121ኛዉ የአድዋ ድል በዓል

ለበዓሉ መታሰቢያ ከአያቴ ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ግጥሞች አንዱን ልኬያለሁ ሲሉ የነጋድራስ እሸቴ ተሰማን ሥነ-ግጥም ያደረሱን የልጅ ልጃቸዉ አቶ ታደለ ይድነቃቸዉ ተሰማ  ናቸዉ። 

ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ሦስቱን ቀለማት፤

እባካችሁ ሰዎች እንዳለ ተዉት፤

ሰሀጢና ጉንደት፣ መተማ፣ አድዋ ላይ ማይጨው ያለቁት፤

ለዚች ባንዲራ ነው መልኳን አታጥፏት።

ነጋድራስ እሸቴ ተሰማ የአድዋን ድል በማስመልከት ከቋጠርዋቸዉ አጫጭር ሥነ-ግጥሞች የተወሰደ  ነዉ።

በእለቱ ዝግጅታችን የአድዋን ታሪክ የሚነግሩንን የታሪክ ባለሞያ ይዘን ዘንድሮ የቱሪዝም ሚኒስቴር የአድዋ ድል በድምቀት እንዲከበር ለማድረግ ያደረገዉን እንቅስቃሴ እንዲሁም ወጣቶቹ የአድዋ ተጓዦች የጎዞአቸዉን መጠናቀቅያ እናያለን ።

Äthiopien Addis Abeba Annual national celebrations Adwa Victoy
ምስል Abel Wabella

ጉዞዋችንን በስኬት አጠናቀናል። የኢትዮጵያ አምላክ ይክበር ይመስገን። በዓድዋ ድል ክብረ በዓል ላይ ተገኝተናል፤ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ የዘንድሮዎቹ የአድዋ አራት ተጓዦች በጠዋት መልክት አድርሰዉናል።  በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን ወደ ዓለም አቀፍ የቅርስ ማኅደር የሚገቡ የኢትዮጵያ የቅርስ አስተዳደር ሰነድ ዝግጅት ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ፤ በአድዋ ታሪክ ላይ የተለያዩ ጽሑፎችን ለአንባብያን አቅርበዋል።  

«ስለ አድዋ ድል ከመናገራችን በፊት ዓድዋ ድል እንዲሆን አልያም የዓድዋ ጦርነት እንዲመጣ ቅድመ ነገሮች ብዙ ናቸዉ። ዓድዋ በራሱ እንደ ጦርነት ሆኖ አልመጣም። የአዉሮጳ ሃያላን መንግሥታት በተለይ አፍሪቃን በተለያዩ የራሳቸዉ የቅኝ ግዛት ክልሎች ዉስጥ ለማዋል፤ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል በዚህም ተስመማምተዋል ። አፍሪቃ ዉስጥ የየራሳቸዉን ድርሻ ተከፋፍለዋል። ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ ግን የስዊዝ ቦይ መከፈት እንዲሁም በቀይ ባህርና አካባቢዉ ጆኦ ፖለቲካ ቀይ ባህርን የመቆጣጠርያ ፤ የአባይን ምንጭ የመቆጣጠር ሂደት ዉስጥ ተደጋጋሚ ጦርነቶች ኢትዮጵያ አካናዉናለች። ከነዚህም አንዱ ከአድዋ ጦርነት በፊት የተደረገዉ የጉራ የጉንደት እንዲሁም ደግሞ ከጣልያን ጋር በሰሃጢና በዶጋሊ የተደረገዉ ጦርነት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ። »

‹‹በ20ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም ትኩረትና ፊቱን ኢትዮጵያ ላይ እንዲያደርግ ካስገደዱት ጥቂት ክስተቶች መካከል አንዱና ዋናው የዓድዋ ድል ነው›› በማለት ታዋቂው የታሪክ ሊቅ ባህሩ ዘውዴ መናገራቸዉ ተዘግቦአል። በዝያን ጊዜ የቅኝ ግዛቶች ቀደዉ ያወጥዋቸዉ አዲስ አካባቢዎች ይላሉ ፤ አቶ ኃይለ መለኮት አግዘዉ በመቀጠል በኢትዮጵያ ላይ ለተከሰቱ በርካታ ጦርነቶች መንሲኤ ለመሆን በቅተዋልም ። አድዋ ከዝያ በኋላ ለነበረዉ አርበኝነት መሠረት የጣለ ድልም ነዉ ሲሉ አቶ ኃይለመለኮት ተክለዋል።  

Äthiopien Addis Abeba Annual national celebrations Adwa Victoy
ምስል Abel Wabella

«በ1879 የዶጋሊ ጦርነት ተደርጎ ጣልያኖችን ባናስወጣም ዶጋሊ የራስ አሉላን ታላቅነት ያስመሰከረና ፤ ለቅን ግዛት አንበረከክም የሚለዉን ያሳየ ነበር። ከዝያ በመቀጠል የነበረዉ ከክዋት ጦርነት የምንለዉ ራስ መንገሻ በኢጣልያኖች ድል የተደረጉበት ጦርነት ነዉ። በኋላም ከአቼ ምኒሊክ ጋር ዉጫሌ ላይ በተደረገዉ ዉል፤ አንቀጽ 17 ኢትዮጵያ በጣልያን ሥር እንደሆነች የሚያሳየዉ ዉል ወደ ጦርነት እንድናመራ ተደርጎአል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጦር ከአዲስ አበባ እስከ ዓድዋ 1066 ኪሎ ሜትር  በመ ጓዝ የኢጣልያን የተቀረዉn የኢትዮጵያን ክፍል የመያዝ ህልም አክሽፎአል። ያ ማለት በተቀሩት አንዳንድ ቦታዎች በምስራቅም ይሁን በሰሜን ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛቶች ቀደዉ ያወጥዋቸዉ ግዛቶች ተፈጥረዋል። መረማመጃም ሆነዉ በኋላ ላይ ኢትዮጵያ ላይ ለተከሰቱ ብዙ ጦርነቶች፤ እንዲሁም አሁን ላይ ላሉት አንዳንድ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ችግሮች መንስዔ ሆንዋል። ነገር ግን ዓድዋ ለኢትዮጵያዉያን ከዝያ በኋላ ለነበረዉም አርበኝነት መሠረት የጣለ ድል ነዉ። የዓድዋ ተራሮች «ማዉንቴን ኮንፈረንስ» ይባላሉ ፤ አካባቢዉ ላያ በትግርኛ አጽበ ጽዮን ይባላሉ፤ የጽዮን ጠባቂ የሚባሉ ተራሮች ናቸዉ ኋላ ላይ ታላቁ የዓድዋ ድል መሠረት የሆኑት። ለዚህm ዓድዋ በጦርነቱ ብቻ አይደለም የሚታወቀዉ ደንደርታን የሃን እና የመሳሰሉትን የዚያ አካባቢ ቦታዎችን ይዞ በዝያ መስመር ያለ ትልቅ የኢትዮጵያ ስልጣኔ መሰረት የሆነም ስፍራ ነዉ። ዓድዋ በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ብዙ ብዙ አበርክቶ ያለ አካባቢ ነዉ። ወጣቱ ኅብረተሰብ በርግጥ ክብረ በዓሉን በብሔራዊ ደረጃ መንግሥት በትልቅ አከባበር እየወሰደዉ ነዉ፤ ተዳክሞና ተቀዛቅዞ ነበር ባለፉት አስር ዓመታት። የዓድዋ በዓልን ብቻ ሳይሆን የካቲት 12 ትክክለኛዉን የሚዲያ ሽፋን ማግኘት አለበት። ወጣቱ የበለጠ ለማድረግ እናም በኢትዮጵያ ዉስጥ አርበኝነትን ሃገር ወዳድነትን ያሰረፀ ታላቅ ስፍራ ነዉና አድዋ ለወጣቱ የነጻነት ፋና፤ የነጻነት ቀንዲል፤ ችቦ የምንለዉ ነዉ ዓድዋ።»    

የአድዋ በዓል አከባበር ዘንድሮ ከምንጊዜዉም በላይ እንዲከበር መስርያቤታቸዉ እንደሰራ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና የአለም አቀፍና  ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ  አባተ ገልጸዉልናል።

Äthiopien Addis Abeba Gedenken Adwa Mitglieder der Veteranen-Vereinigung
ምስል DW/Getachew Tedla

እንኳን ለአድዋ በዓል አደረሳችሁ ሲሉ ወደ ጣብያችን ስልክ የደወሉት በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆኑትና በዓለም አቀፉ ኅብረት ለፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ተጠሪና የጣልያን መንግሥት ለኢትዮጵያ ካሳ እንዲከፍል በመሟገት ላይ የሚገኙት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ ለ 80ኛ ጊዜ በተከበረዉ የሰመአታት ቀን መታሰብያ ጠቃሚ ሁኔታዎች መከሰታቸዉን ገልፀዋል።  

በልዩ የዓለም ከተሞች በፀሎት በስብሰባ ብሎም የተቃዉሞ ሰልፎች የሰመዓታት ቀን መታሰቡን ኢጣልያ ለኢትዮጵያ ካሳ መክፈል አለባት ሲሉ የሚወተዉጡት አቶ ኪዳኔ አለማየሁ ገልፀዋል። ይህን የካሳ ጥያቄን በተመለከተ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና የአለም አቀፍና  ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ  አባተ ያላቸዉን አስተያየት ጠይቀንም ነበር፤

«121ኛው» የዓድዋ ድል ክብረ በዓል ከሶሎዳ ተራራ ግርጌ ያከበሩት የአድዋ አራት ተጓዦች ከትናንት በስትያ የሓ ከተማ ሲደርሱ በጉዞ ማስታወሻቸዉ ላይ እንደከተቡት የ5ሺህ ዓመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችው ጥንታዊቷ የዳዕማት ስልጣኔ መዲና የሓ ከተማ ገብተናል። ዳግማዊ አጼ ምኒልክ በዚህ ቦታ ላይ በዓድዋ ድል ዋዜማ የካቲት 22 ቀን ሁለት የብስራት ዜና ሰምተዋል የነ ተሰማ ናደውን የአውሳ ጦርነት ድል እና የራስ ስብሐትን ጣሊያኖችን ከድቶ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል። በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን ወደ ዓለም አቀፍ የቅርስ ማኅደር የሚገቡ የኢትዮጵያ የቅርስ አስተዳደር ሰነድ ዝግጅት ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ፤ ሚኒሊክ ከአድዋ ድል በኋላ የሃገርን ህልዉና በማስጠበቅ ከተሞችን በመስረት ያቆዩልን ሥራ ትዉልድ ሁሉ ሊዘክረዉ ይገባል እቴጌ ጣይቱም ታሪክ ሕያዉ ሆኖ የሚወሳ ነዉ።  

Äthiopien | Reise zum Gedenktag der Schlacht von Adwa: Guzo Adwa
ምስል Addis Standard/Y. Shumete

«121ኛው» የዓድዋ ድል ክብረ በዓል ከሶሎዳ ተራራ ግርጌ ያከበሩት የአድዋ አራት ተጓዦች ከትናንት በስትያ የሓ ከተማ ሲደርሱ በጉዞ ማስታወሻቸዉ ላይ እንደከተቡት የ5ሺህ ዓመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችው ጥንታዊቷ የዳዕማት ስልጣኔ መዲና የሓ ከተማ ገብተናል። ዳግማዊ አጼ ምኒልክ በዚህ ቦታ ላይ በዓድዋ ድል ዋዜማ የካቲት 22 ቀን ሁለት የብስራት ዜና ሰምተዋል የነ ተሰማ ናደውን የአውሳ ጦርነት ድል እና የራስ ስብሐትን ጣሊያኖችን ከድቶ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል። በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን ወደ ዓለም አቀፍ የቅርስ ማኅደር የሚገቡ የኢትዮጵያ የቅርስ አስተዳደር ሰነድ ዝግጅት ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ፤ ሚኒሊክ ከአድዋ ድል በኋላ የሃገርን ህልዉና በማስጠበቅ ከተሞችን በመስረት ያቆዩልን ሥራ ትዉልድ ሁሉ ሊዘክረዉ ይገባል እቴጌ ጣይቱም ታሪክ ሕያዉ ሆኖ የሚወሳ ነዉ  

ባልተለመደ መልኩ  የአድዋ ክብረ በአል ላይ የተጋበዙት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ታምቦ ኢምቤኪ ዛሬ በአድዋ ከተማ ላይ በተከበረዉ ደማቅ ዝግጅት ላይ ተገኝተዉ  «የአድዋ ድል በዓልን የመላው አፍሪቃ  ሀገራት በዓል ማድረግ ይቻላል ሲሉ መናገራቸዉ ተዘግቦአል። አድማጮች መልካም በዓል እያልኩ ለቃለ ምልልሱ የተባበሩን እያመሰገንን ሙሉ መሰናዶዉን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ