1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

17ኛዉ የዓለም ኤድስ ጉባኤ በሜክሲኮ

ሰኞ፣ ሐምሌ 28 2000

በሜክሲኮ 17ኛዉ የዓለም ኤድስ ጉባኤ ትናንት ተከፍቷል።

https://p.dw.com/p/EqJL
በፈቃደኝነት የሚመረመሩት በርክተዋል
በፈቃደኝነት የሚመረመሩት በርክተዋልምስል dpa

የሰዎችን ህይወት እየተፈታተነ የሚገኘዉ የHIV ቫይረስ ከታወቀ ከ27ዓመታት ወዲህ የመረጃ ስርጭት፤ በሽታዉን የመከላከልና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የቫይረሱ ተጠቂዎች መድሃኒትም ሆነ ህክምና የማዳረሱ ጥረት ቀጥሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ወገኖች እንደተናገሩት ግን ይህ ሁሉ ርብርብ በተለይም የድርጅቱን የምዕተ ዓመት የልማት ግብ ለማሳካትና የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ የአቅም እጥረት እየታየ ነዉ። በአንፃሩ ኢትዮጵያን መሰል በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዱ አገራት ይዞታ ከዚህ አኳያ መሻሻል ያሳዩ ሲሆን እስከአዉሮጳዉያኑ 2010ዓ,ም ድረስም ሊደርሱበት ካለሙት ግብ ለመገኘት መፍጨርጨር ይዘዋል።