1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብዙዎች ዓመቱ ፈታኝ እንደነበር ይስማማሉ

እሑድ፣ ጳጉሜን 5 2009

ከሁለት ቀናት በኋላ አሮጌዉ ተብሎ የሚጠራዉ 2009 ዓ,ም ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ከባድ ዓመት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ከእሱ ቀድሞ ካለፈዉ 2008ዓ,ም የወረሳቸዉን የፖለቲካ  እና ማኅበራዊ  ቀዉሶች ተሸክሞ የባለፈዉ ዓመት ከ10 ወራት በላይ መላ ሀገሪቱን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር አክርሟል።

https://p.dw.com/p/2jcGH
Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

ተሰናባቹ 2009 ዓ.ም ሲቃኝ፥ ውይይት

ለበዓል አደባባይ የወጣ በርካታ ሕዝብ ለሞት፣ ለጉዳት እና እስራት ተዳርጎበታል። የቆሻሻ ክምር ተንዶም ሕይወት ጠፍቶበታል። የድንበር መካለል ግጭቶች፣ የማንነት ጥያቄዎች በተለያዩ አካባቢዎች አስተናግዷል። ይህም ሆኖ ዉይይትና ድርድር፣ ጥልቅ ተሐድሶ እና ሹም ሽርም ተነግሮበታል። ነጋዴዎች ላይ የተጣለ የገቢ ግብር ያስከተለዉ ተቃዉሞም የታየዉ በዚሁ ዓመት ነዉ። ዶቼ ቬለ አዲስን ዓመት ከመቀበል አስቀድሞ 2009ዓ,ም እንዴት ነበር ብሎ ዉይይት አካሂዷል። ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ