1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

4 የአየር ኃይል አብራሪዎች ኮበለሉ መባሉ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 2007

በአንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኀን እንደተዘገበውና የኢትዮጵያ መንግሥትም እንዳረጋገጠው Mi-35 በሚል መለያ በሚታወቅ አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ፣ 3 ኢትዮጵያውያን የአየር ኃይል ባልደረቦች፤ ከድሬዳዋ ኮብልለው ኤርትራ ገብተዋል። ይህ የሆነው ከ

https://p.dw.com/p/1EEMS
ምስል DMITRY KOSTYUKOV/AFP/Getty Images

13 ቀን ገደማ በፊት ሲሆን ፤ ከሰሞኑም ሌሎች 4 የአየር ኃይል አባላት ኬንያ ገብተው ተገን መጠየቃቸው ተወርቷል። ስለዚህ ጉዳይ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል መረጃም ሆነ ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት አድርገን ነበር ፤ ማግኘት ግን አልቻልንም። በኬንያ መገናኛ ብዙኀን ፤ በጋዜጣ፤ ራዲዮም ሆነ ቴሌቭዥን ምናልባት የተወሳ ነገር አለ ወይ በማለት ፣ አጠያይቀን ነበር ።

Russland Kampfjet Sukhoi Su-27
ምስል Piotr Polak/AFP/Getty Images)

ሻምበል ሳሙኤል ግደይ የተባሉት አብራሪ ከ 2 ባልደረቦቻቸው ጋር Mi 35 በተሰኘው የጦር ሄሊኮፕተር ኮብልለው ከኢትዮጵያ መውጣቸው በተነገረ በአንድ ሳምንት ገደማ ውስጥ 4 የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ፤ ወደ ኬንያ በመኮብለል በዚያ የፖለቲካ ተገን ጠየቁ መባሉ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። የጋዜጠኞች መሳደድ ፤ እሥራትና የመሳሰለው ነበር በሰፊው ሲያነጋግር የቆየው፤ አሁን ወታደሮች ፤ እዚህም ላይ የጦር አኤሮፕላን አብራሪዎች ኩብለላ በቀጣይነት መካሄዱ ፣ ምክንያትን የሚያጠያይቅ ይሆናል። ምላሹን ከራሳቸው፣ ከኮብላዮቹ አንደበት መስማት እስኪቻል ድረስ! ይሁንና ፣ 4 የአየር ኃይል ጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ኬንያ ገቡ ስለመባሉ በዚያች ሀገር መገናኛ ብዙኀን የተገበ ጉዳይ ይኖር ይሆን ፣ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ----

ጋዜጠኞች ይጽፋሉ ይናገራሉ ፤ ያስተምራሉ ሒስ ይሠነዝራሉ፤ አግባብነት ባለው ጉዳይ ላይ! ሙያቸው ነውና! ዴሞክራሲ በሠፈነባቸው አገሮች ፣ ለሕብረተሰብ ብቻ ሳይሆን በሥልጣን ላይ ለሚገኝ መንግሥትም ተፈላጊዎች ናቸው! ።

በአንድ ሀገር ሕብረተሰብ ውስጥ ነጻ የሐሳብ ልውውጥ ሲኖር ለሀገርም ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽዖ አለውና! ዴሞክራሲን ከልብ ባልተቀበሉ ፤ ወይም የዴሞክራሲ ጸር በሆኑ አገሮች ግን ጋዜጠኞች እንደ እክል መታየታቸው የታወቀ ነው። የጋዜጠኞችን ያህል በቀጥታ የማያጋፈጡ ወገኖች ተቃውሞን በኩብለላ ሲገልጹ ምን ማለት ይቻላል? ምን የከፋ ችግር ቢያግጋጥም ይሆን?

ኬንያና ኢትዮጵያ ፣ በመከላከያ የጋራ ትብብር ውል የተፈራረሙ አገሮች ናቸው። ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አንስቶ የቀጠለ ጉዳይ ነው። የጦር ኃይል አባል የሆነ ሰው ከብልሎ ኬንያ ቢገባና ተገን ቢጠይቅ አደጋ ይኖረዋል?

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ