1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

50ኛ አመት የበርሊን ግንበታ መታሰብያ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 12 2003

«የግንቡ ታሪክ መጨረሻ ለኛ ትልቅ ብርታትን ሊሰጠን ይችላል። የዚህንም ታሪክ መጨረሻ የፃፈዉ ህዝብ ነዉ። ግንቡ ተናደ እንጂ አልፈረሰም።»

https://p.dw.com/p/Rg4Y
ምስል picture alliance/ZB

ሲሉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የጀርመኑ ርዕሰ ብሄር ክርስታያን ዎልፍ ምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመንን ለሁለት ከፍሎ የነበረዉ የበርሊኑ ግንብ መገንባት የጀመረበትን 50ኛ አመት መታሰብያ በማስመልከት ንግግር አሰምተዋል። ልክ የዛሪ ሃምሳ አመት እ.ጎ.አ ነሐሴ 13 ,1961 አ.ም የሶሻሊስት ርዕዮተ አለምን አራማጅ የነበረዉ የቀድሞዉ ምስራቅ ጀርመን መንግስት በርሊንን ለሁለት የከፈለዉን ግንብ መገንባት የጀመረበትን እና የብዙሃን ህዝብ ህይወት የተቀጠፈበት ግንብ ጀርመናዉያን በሃዘን አስታዉሰዉታል። የበርሊኑ ግንብ በቆመበት አካባቢ በተለይም በቤርናወር ጉዳና አካባቢ በተካሄደዉ ስነ-ስርአት ላይ የአገሪቱ ፕሪዝደንት ክርስትያን ዎልፍ፣ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፣ የዉጭ ጉዳይ ምኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የቀድሞ የመስራቅ ጀርመን መንግስት ተቃዋሚዎች እንዲሁም በዚሁ የበርሊኑን ግንብ ተሻግረዉ ለማለፍ ሲሉ የተገደሉ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ