1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

8ኛው የዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ

ሰኞ፣ ሰኔ 15 2007

የዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅ ፔተር ሊምቡርግ ዛሬ 8ኛውን የዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ከፈቱ። በዚህ መድረክ 2000 የሚጠጉ ሰዎች ተካፋይ ሆነዋል።

https://p.dw.com/p/1Flmh
GMF 2015 Eröffnung Peter Limbourg und Monika Grütters Sendestart
ምስል DW/H. Mund

[No title]

የዘንድሮው ዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙኃን ጉባኤ ዋና ትኩረት ባለንበት በዲጂታል ዘመን የመገናኛ ብዙኃን በውጭ ፖለቲካ ላይ የሚጫወተው ሚና ይሆናል። ሊምቡርግ « በዓለም ዙሪያ በዲጂታል መረጃዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ እየሆንን መጥተናል» ብለዋል በመክፈቻ ንግግራቸው። ለሶስት ቀናት የሚዘልቀው 8ኛው የዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ዛሬ ሲከፈት፤ እንደ ከዚህ ቀድሞው ሁሉ በርካታ ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ የመገናኛ ብዙኃን ባልደረቦች እና ፖለቲከኞች ተገኝተዋል። በዶይቸ ቬለ ዋና ስራ አስኪያጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ መድረኩን የከፈቱት ፔተር ሊምቡርግ፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂ በተስፋፋበት በዚህ ዘመን እንኳ ጥራት ያለው ጋዜጠኝነትን መተግበር አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል።« ይህ የሆነበት ምክንያት አንዳንዴ ከእውቀት ማነስ ፤ አንዳንዴ ደግሞ ከገንዘብ እጥረት፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው ለህትመቱ መቀነስ ምክንያት የሆኑት።»

በዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ግልፅ መልዕክት ነው የተላለፈው ፤ መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ነፃነት እና መብት እንደሚያሻቸው። ለዚህም ማሳያ የሳውዲው የኢንተርኔት ፀሃፊ ራይፍ በዳዊ የዶይቸ ቬለን« የመናገር ነፃነት ሽልማት» አግኝቷል ። በደዊ ሃሳባቸውን በግልፅ በመናገራቸው የታሰሩና የሚሰቃዩ ሰዎች ምሳሌ ሆኗል ። ታድያ እነዚህ እና ሌሎች ፈተናዎች የተጋረዱባቸው መገናኛ ብዙኃን በዘመናዊው እና በዲጅታሉ ዓለም እንዴት እንደሚቀጥሉ መወያየት ያስፈልገዋል። ስለሆነም የዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ የበኩሉን ድርሻ እተወጣ መሆኑን አስታውቋል ። ከ 100 ሀገራት የመጡ ፤ በርካታ ጋዜጠኞች በጉባኤው ላይ ተካፍለዋል።

GMF 2015 Media Summit If it bleeds, it leads
ምስል DW/M. Magunia

በዚህ ጉባኤ ዶይቸ ቬለን ሁለት አዳዲስ አገልግሎቶቹን አስተዋውቋል። ከነዚህም አንዱ በዘመናዊ ስልኮችና ታብሌቶች እንዲሁም ኮምፕዩተሮች ላይ በነፃ የዓለም ዜናን ማግኘት የሚያስችለው የ DW APP ወይም አፕሊኬሽን ነው ። ይህ አገልግሎትም የዶይቸ ቬለን ተከታታዮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ተሳታፊ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም ዶይቸ ቬለ ከዛሬ ጀምሮ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚያስተላለፈውን የቴሌቪዥን ፕሮግራምወደ 24 ሰዓት ከፍ አድርጓል። የስርጭቱም ትኩረት አፍሪቃ እና እስያ ናቸው ።

« አውሮፓ ውስጥ እንደሚገኝ ፣ አንድ ዲሞክሪያሲያዊ ሀገር የአውሮፓ እሴቶች የበለጠ በግልፅ እንዲታዩ እንፈልጋለን። ስለሆነም ይህን የእንግሊዘኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመጀመር የራሳችንን ዋና ድርሻ እንወጣለን።»በጀርመን ፌደራል የባህል እና የመገናኛ ሚኒስትር የሆኑት ሞኒካ ግሩተርስ በዚህ ጣቢያ አማካይነት በርካታ ሰዎች ከጀርመን ተጨባጭ መረጃ ሊደርሳቸው ይችላል ብለዋል። አክለውም፤« ዶይቸ ቬለ ዲሞክራሲያዊ የሰፈነበትን የሀገራችንን ገፅታ ያሳያል፤ በተለይ ደግሞ ቀውስ በተንሰራፋባቸው ሀገራት እና በአምባ ገነን ስርዓት ስር ያሉ በርካታ ሰዎች ፣ ዶይቸ ቬለን ከነፃው ዓለም ጋር እንደመገናኛ ይቆጥሩታል»

ሚኒስትር ግሩተርስ ከዚህም ሌላ ትኩረት ያሻሉ ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል። ከነዚህ መካከል ከዲጂታል ቴክኖሎጂው ጋር በተያያዘ ሀሳብን በነፃ ለመግለፅ አደጋ ይሆናል ያሉት ነው። « በዲጂታል አገልግሎት የምናቀርባቸውን መንገድ እያሳዩን እና ስለ ይዘቱ እየወሰኑ ያሉት ትላልቅ የኢንተርኔት ኩባኒያዎች ናቸው ፤ ይህም ግልፅ ባልሆነ መንገድ እና መስፈርት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የግል መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ተገዢ መሆን የለብንም። »

GMF 2015 What is media viability and how is it relevant to foreign policy
ምስል DW/M. Müller

ይህ እንዴት ሊስተካከል እንደሚችል 8ኛው የዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ ታዳሚዎች ከሚመክሩበት ርዕስ አንዱ ነው። እስከ ዕሮብ በሚቆየው ጉባኤ ጎን ለጎን 40 ዓውደ ጥናቶች ይካሄዳሉ። ዲጂታል ቴክኖሎጂ የአለም አቀፉን ግንኙነት እንዴት ይቀይራል? እና ኢንተርኔት አለአግባብ ለፅንፈኞች ፕሮፖጋንዳ መዋሉን እንዴት መከላከል ይቻላል? የሚሉት ጥያቄዎች በመድረኩ ። መልስ ከሚያፈላልግላቸው ጥያቄዎች ጥቂቶቹ ናቸው።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ