1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

9 የተቃውሞ ፓርቲዎች ስምምነት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2007

ኢትዮጵያ ውስጥ ፤ ከገዥው ፓርቲ የተለየ አማራጭ የፖለቲካ አጅንዳዎች ይዘው የቀረቡ 9 የተቃውሞ ፓርቲዎች፤ በሚያስሟሟቸው ጉዳዮች ተባብረው ለመሥራት መስማማታቸው ተገለጠ።

https://p.dw.com/p/1Da1a
Pressekonferenz Äthiopien Parteien,
ምስል DW

ተባብረው ለመሥራት የተፈራረሙት ፓርቲዎች፤ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤(መኢአድ) የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት(መአሕድ)፤ መአዴፓ ሰማያዊ ፓርቲ፤ የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ዴሞካራሲያዊ ድርጅት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ፤ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት የከምባታ ሕዝብ ኮንግረስ ናቸው።

የትብብሩ አመራር አባላት፤ ከዚህ ቀደም የነበሩ ጥምረቶችን ድክመቶች በመፈተሽ፤ በጋራ ለመሥራት ሲስማሙ፤ ከዚህ ቀደም የተቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ መተቸትን የማይቀበሉ ነበሩ። በነጻው ፕረስ ሳይቀር ተቃዋሚዎችን መተቸት ኢ ህ አ ዴ ግ ን ያጠናክራል የሚል አስተሳሰብ ነበረና ይህን አስተሳሰብ ሰብረን ወጥተናል ማለታቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ