1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

AGOA ለአፍሪቃ የቀረበዉ የንግድ እድል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2001

ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሀገራት ከቀረጥና ኮታ ነፃ ሸቀጦች ወደአሜሪካ እንዲያስገቡ የሚፈቅደዉ AGOA በመባል በእንግሊዝኛ ምህፃር የሚታወቀዉ ዉልን የተመለከተ ስምንተኛ ጉባኤ ባለፈዉ ሳምንት ኬንያ ናይሮቢ ላይ ተካሂዷል።

https://p.dw.com/p/J8VZ
የኦባማ ቪዲዮ መልዕክትምስል AP

መስፈት አሟልተዉ የዚህ ዉል ተጠቃሚ የሆኑ የአፍሪቃ ሀገራትና አሜሪካ በየጊዜዉ እየተገናኙ ይመክራሉ። በዚህኛዉ ጉባኤ ላይ አዲሷ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የንግድ ልዑካንን አስከትለዉ ተሳትፈዋል። AGOA ለአፍሪቃ ሀገራቱ ጠቀሜታ እንዳለዉ ብዙዎች ቢናገሩም አሜሪካም ጥሬ አላባ የምታገኝበት መንገድ ነዉ የሚሉት አልጠፉም።

አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ