1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

HRW ያወገዘው የግብፅ ዕርምጃ

ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2002

ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የግብፅን ድንበር አቋርጠው ወደ እስራኤል ለመሻገር የሞከሩ በርካታ ስደተኞች በድንበር ጠባቂዎች ተተኩሶባቸው ተገድለዋል ።ከነዚህም አብዛኛዎቹ ኤርትራውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች ናቸው ።

https://p.dw.com/p/MHtx
የሲና በረሀምስል picture-alliance / dpa

ዘቦቹ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ሊያቋርጡ ሲሞክሩ ያዝናቸው የሚሏቸውን ስደተኞች ተኩሰው የሚገድሉት እጃቸውን ላለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ መሆኑን የግብፅ ባለስልጣናት ይናገራሉ ። ይሁንና ይህ የግብፅ ወታደሮች ዕርምጃ በሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በእጅጉ እየተወገዘ ነው ። የግብፅን መንግስት ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል የሚኮንነው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ Human Rights Watch ግብፅ ዓለም ዓቀፍ ግዴታዎቿን እየጣሰች ነው ሲል ይከሳል ። በድርጅቱ የግብፅና የሊቢያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ አጥኚ ሄባ ሞራየፍን የነጋገረችው ሂሩት መለሰ ዝርዝሩን አጠናቅራለች ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ