1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

IOM ለተመላሾች ተጨማሪ እርዳታ መጠየቁ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 11 2006

በፍልሰት ሳቢያ በሚከሠቱ ችግሮች ላይ በማትኮር የተለያዩ አጣዳፊ የርዳታ ዓይነቶችን የሚያቀርበው ዓለም አቀፍ ድርጅት (IOM) ከስዑዲ ዐረቢያ ተገደው የተመለሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ላይ ሲሆን የተረጂዎቹ ቁጥር ከፍ በማለቱ ተጨማሪ እርዳታ እንዲቀርብለት መማጸኑ ተመልክቷል።

https://p.dw.com/p/1AeJs
Saudi Arabien Riad Unruhen
ምስል AFP/Getty Images

ካለፈው ኅዳር 4 ቀን 2006 ዓ ም ፣ ወዲህ እስከ ከትናንት በስቲያ ፣ ወደ 140 ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደ ትውልድ አገራቸው መመለሳቸውን IOM አስታውቋል። ከስዑዲ ዐረቢያ እንዲወጡ የተገደዱ፣ በተጨማሪ 35 ሺ ኢትዮጵያውያን ከሪያድ፤ ጅዳና መዲና እንደሚመለሱ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትና IOM ይጠብቃሉ።

IOM እስካሁን ምን እንዳደረገና በማድረግም ላይ እንዳለ በኢትዮጵያ የድርጅቱን (IOM)የመገናኛ ጉዳይ (ኮሙዩኒኬሽንስ)ባለሙያ አቶ ዓለማየሁ ሠይፈ ሥላሴን ጠይቀናቸው ነበር።

ብዙዎቹ ተመላሾች፤ ስዑዲ ዐረቢያም በነበሩበት ጊዜ ሲናገሩ እንደተሰማው፣ ባስቸኳይ እንዲወጡ ስለተገደዱ፣ ንብረታቸውን በቅጡ ለመሰብሰብ ጊዜ አላገኙም ሁኔታው አላመቻቸውምና! ንብረታቸው የተዘረፈባቸውም ጥቂቶች እንዳልሆኑ ነው የተሰማው። IOM ከጊዜያዊ መስተንግዶ ሌላ እንዚህን በግዴታ የተመለሱ ሰዎች በማቋቋም ረገድ የሚያደርገው ተሳትፎ እስከምን ድረስ ይሆን--

ቁጥራቸው እንደተጠቀሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመለሱት ሰዎች በዛ ያሉ ናቸው። እነዚህ ወገኖች ለመርዳት ወደፊትም ከተለያዩ አገሮች የሚመለሱ ሊኖሩ ይችላሉና በኢትዮጵያ ፣ ዓለም አቀፉ IOM ድርጅት ተፈላጊውን ርዳታ ለማቅረብ አቅሙ አንዴት ነው?

በአካልም በመንፈስምየተጎዱ ሰዎች አሉና እነዚህን ሰዎች በህክምናም ረገድ ለመርዳት ወደ ተለያዩ ክፍላተ ሀገር የሚጓዙትንም ለማሣፈር አቅምና ዝግጅቱ እስከምን ድረስ ይሆን?

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ