1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

RSF ሞቱ ያላቸው ኤርትራውያን ጋዜጠኞች

ዓርብ፣ ነሐሴ 25 2004

ኤርትራ ውስጥ ከ10 ዓመታትበላይ በእስራት ከነበሩጋዜጠኞች መካከል3 ምናልባትም 4ቱ ሳይሞቱ አልቀሩም ሲል ዋናጽ/ቤቱ በፓሪስ፣ፈረንሳይየሚገኘው፤ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት ትናንት ማስታወቁ የሚታወስ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ከኤርትራ

https://p.dw.com/p/161lk
ምስል AP Graphics/DW

መንግሥት ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም፤ ይሁንና ዜናውን ይፋ ያደረገውን የ  RSF  አፍሪቃ ክፍል ኀላፊና አንድ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ተጠሪ   አነጋግረናል ።

Issaias Afewerki, Präsident von Eritrea
ምስል picture-alliance/dpa

3 ኤርትራውያን  ጋዜጠኞች ምናልባትም 4  ፤ በእሥራት  ላይ እንዳሉ ህይወታቸው አልፏል ሲል ዋና ጽ/ቤቱ በፓሪስ ፤ፈረንሳይ ፣ የሚገኘው ድንበር አያግዴው ፣ ለጋዜጠኞች መብት ታጋይ ድርጅት(RSF)                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                               መግለጫ ማውጣቱ የታወቀ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጥያቄአችን፣ ይህን እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? የሚል ነበር። የድርጅቱ የአፍሪቃ ክፍል ኀላፊ ፣ አቶ («መስዬ») አምብርዋ ፒዬር፣ ---«ለቀረበው ዜና የመጀመሪያው ምንጭ እኛ ነን፣ ይፋ ለማድረግ የምንወስነው ስለሆነ ነገር መቶ-በመቶ እርግጠኞች ስንሆን ነውና በዚህ አይጠራጠሩ! በእኛ ይሁንበዎት!ጥያቄዎ ገብቶኛል። ይህን የመሰለውን ዜና ፤ በኤርትራ ለማጣራት እጅግ ከባድ ነው። ነገር ግን ባለፉት ሳምንታትና ወራት  ስናደርግ የከረምነው፤ የተሰጡ የምሥክርነት ቃላትን ፣ ደጋግመን በመስቀልኛ ጥያቄ(ምርመራ) ስናጣራ ነው። ይህንንም ዜና ኤርትራ ውስጥ ከሚገኙ ሰዎችና በቅርቡ ኤርትራን ለቀው ከወጡ የእሥር ቤት ዘበኞች ነው ያገኘነው።

Straßenszene in der Independence Avenue in Asmara, Eritrea
ምስል picture-alliance/ dpa

አፅንዖት ሰጥቼ እዚህ ላይ መናገር የምፈልገው የወህኒ ቤት ዘበኞቹና ሌሎቹ፣ የተናገሩትን መርምረን 3 ቱ ጋዜጠኞች በኢራዕይሮ ማጎሪያ ማዕከል ሞተዋል ከሚለው መደምደሚያ ነው የደረስን። 3 ቱም ተይዘው በእሥር የቆዩት ፣ እ ጎ አ ከ 2001 አንስቶ ነው።»

የኤርትራ መንግሥት፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠን ሞክረን/ጠይቀን ፣ አልተሣካልንም።

ኤርትራ የ ተ መ ድ  እና የሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናትና፤ ለምሳሌ ቀይመስቀልም ሆነ፣ ሌላ የሰብአዊ መብት ድርጅት እሥረኞቹን እንዲጎበኝ እንድትፈቅድ ለማድረግ አይቻልም ወይ?

«ይህን ለማድረግ አጋጣሚው መኖሩ ብቻ ሳይሆን እና እንደምንለው፣ ኤርትራ መሠረታዊ ነጻነትንና ሰብአዊ መብትን እንድታከብር ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ እርምጃ መውሰድ ያለበት ጊዜው አሁን ነው። ሐቁን እንናገር፤ እስካሁን ሲደረግ የነበረው በቂ አይደለም። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ በኤርትራ ያለው ሁኔታ የቱን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ አልተገነዘበውም። ለፕረስ ነጻነት ወይም ሰብአዊ መብት በአጠቃላይ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኤርትራ መንግሥት ላይ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል።»

Blick über die Häuser von Asmara, Independence Avenue
ምስል picture-alliance/ dpa

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር በኤርትራ ወኪል አለው እና እስረኞቹን ዐይቶ  አያውቅም ማየት አይችልም? ከጀኔቡ የማኅበሩ የምሥራቅ አፍሪቃ የፕረስ ጉዳይ ኀላፊ ዣን ኢቨ ክሌሜንዞ፣---

«ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ፣ ማንኛውም  ኤርትራዊ  እሥረኛ ጎብኝቶ አያውቅም መጎብኘትም አይችልም።»

ግን !ለምን? ስለተከለከላችሁ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አላችሁ?

«እስካሁን አልጎበኘንም፤ ወደፊትም ማንኛውንም ኤትራዊ እሥረኛ  አንጎበኝም። ይህን ቃለ ምልልስ ማቆረጥ ይኖርብናል፤ ምክንያቱም 3 ጊዜ ነግሬዎታለሁ፤ በኤርትራ እሥረኞችን አልጎበኘንም፤ አሁንም ቢሆን አንጎበኝም።»

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና የፕረስ ተቋማት የሚሉትን ፣ መንግሥታት በቸልተኝነት ካዩት፤ ድርጅቶችም ከፈሩ፣ ባፋጣኝ አወንታዊ ውጤት የማየቱ ዕድል የጨፈገገ ነው የሚመስለው።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ