1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መድኃኒትን ያለአግባብ ማጓጓዝና መሸጡ አደገኛነቱ ያመዝናል፤

ማክሰኞ፣ ግንቦት 15 2009

መድኃኒቶች ፈዉስ እንዲያስገኙ የሚፈለጉ ለሰዉነታችን ግን ባዕድ የሆኑ ቅምሞች ናቸዉ። በዚህ ምክንያያትም በራስ ፍላጎት ሳይሆን በትክክለኛዉ የህክምና ባለሙያ ታዝዞ የሚወሰድ መድኃኒት ፍቱንነቱ ባብዛኛዉ አይጠረጠርም። በተቃራኒም የጎንዮሽ ጉዳትም ሊያስከትል ይችላል። ለዚህም ነዉ ጥንቃቄ የሚያስፈልገዉ።

https://p.dw.com/p/2dSCQ
Symbolbild Tabletten Pillen Medikament
ምስል Colourbox

መድኃኒትን በጥንቃቄ፤

መድኃኒት በራስ ፍላጎት ሳይሆን በትክክለኛዉ ባለሙያ ታዝዞ ሲወሰድ ፍቱንነቱ ባብዛናዉ አይጠረጠርም። መድኃኒት ፈዉስን ለማስገኘት ጥቅም ላይ ይዋል እንጂ ያልተጠበቀ የጎንዮሽ ጉዳትም ይዞ ብቅ የሚልበት ጊዜ ያጋጥማል። የፋርማሲ ባለሙያዉ አቶ ዘላለም ዘሪሁን የፋርማሲ ባለሙያዉ ስለመድኃኒቱ በቂ ማብራሪያ ሊሰጥ እንደሚገባ፣ መድኃኒቱን ከሚወስደዉ ግለሰብም በቂ መረጃ ሊወስድ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከአንድ ዓመት በፊት በዝግጅታችን መድኃኒቶች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዴት ተገዝተዉ እንደሚገቡ ከኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒት እና ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን፤ የሚመለከታቸዉን ኃላፊ ማብራሪያ ማቅረባችን ይታወስ ይሆናል። በወቅቱ ያነጋገርናቸዉን የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሔራን ገርባን ዛሬም በድጋሚ የዲላዉ አድማጫችን የገጠማቸዉን በመጥቀስ የሚሉን ካለ ስንጠይቅ አላመነቱም። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ