1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሜርክል ዳግም በመራሒተ መንግሥትነት ተመረጡ

ረቡዕ፣ መጋቢት 5 2010

ላለፉት 12 ዓመታት  በመራሒ መንግሥትነት ያገለገሉት አንጌላ ሜርክል ለተጨማሪ አራት ዓመታት ዘመነ ሥልጣን  ተመርጠዋል። መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እንደተፈራዉ ሳይሆን በ 364 የምክር ቤት አባላት ድምፅ  ነዉ የተመረጡት።

https://p.dw.com/p/2uJGr
Deutschland Vereidigung der Bundeskanzlerin
ምስል Reuters/K. Pfaffenbach

አንጌላ ሜርክል የ364 የብዙኃን ድምፅን አግኝተዉ ነዉ የተመረጡት።

 

ላለፉት 12 ዓመታት  በመራሔ መንግሥትነት ያገለገሉት አንጌላ ሜርክል ለተጨማሪ አራት ዓመታት ዘመነ ሥልጣን  ተመርጠዋል። መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እንደተፈራዉ ሳይሆን በ 364 የምክር ቤት አባላት ድምፅ  ነዉ የተመረጡት። አንዳንድ የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ አባሎች ድርጅታቸዉን ለማናደድ መራጮቻቸዉንም ለማስደሰት በዛሬዉ ምርጫ ድምፃቸዉን ይነፍጋሉ ተብሎ ተገምቶም ነበር። ሜርክል ከካቢኔ አባሎቻቸዉ ጋር ለሃገር ጥቅም፤ ህዝብ እና ለሃገሪቱ ደህንነት እስከ መጨረሻዉ ድረስ ለመስራት  ቃለ ገብተዋል።አንጌላ ሜርክል ማን ናቸዉ ? ከምን ተነስተዉ እዚህ ቦታ የደረሱት? በመጭዉ አራት አመት የስልጣን ዘመናቸዉ ምን አዲስ የፖለቲካ ግብ ይኖራል ? የዶቼ ቬለዎቹ ይልማ ኃይለሚካኤልና ቢንያሚን ክኔት ዘገባ አዘጋጅተዋል ይልማ ያቀርበዋል።  

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ