1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን 

ሐሙስ፣ የካቲት 15 2010

በዛሬዉ ዕለት ኢትዮጵያዉያን በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉን ሕዝባዊ አመፅ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተዉጣጡት ተሳታፊዎች መገኘታቸዉን ለዶቼ ቬለ የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪ በሀገሪቱ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም እንደሚቃወሙ አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/2tARc
Ethiopians Demo in Berlin  opposing EU’s deal with African dictators to send back asylum seekers
ምስል Yelma Hinz

ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን 

ለኢትዮጵያ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎች የሚያደርገዉ የጀርመን መንግሥትም አዋጁ እንዲነሳ እንዲጠይቅ፤ እንዲሁም ከአዉሮጳ ሃገራት ጋር በምስጢር ተደርጓል ያሉት ስደተኞችን ወደኢትዮጵያ የመመለስ ስምምነትም ተግባራዊ እንዳይሆን እንዳሳሰቡም አስረድተዋል። ሰልፉን በስፍራዉ ተገኝቶ የተከታተለዉ ይልማ ኃይለ ሚካኤል ተሰላፊዎቹን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ