1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳዑዲ የኢትዮጵያዊያን ስጋት እና የመንግስት ምላሽ

ዓርብ፣ መስከረም 12 2010

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የጣለው የነፍስ ወከፍ ክፍያ በግዛቲቱ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንን አስደንግጧል። በርካቶቹ ነገ ሊመጣ የሚችለዉን በመፍራት ልጆቻቸውን ወደ ሀገር ቤት እየላኩ ነው። ቀሪዎቹ ደግሞ ከነቤተሰቦቻቸው ጠቅለው ወደኢትዮጵያ ለመግባት መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ይጠይቃሉ።

https://p.dw.com/p/2kXh8
Äthiopische Gemeinschaft in Saudi Arabien
ምስል DW/Sileshi Shibiru

የአብዛኞቹ አማራጭ ወደሀገር መመለስ ይመስላል፤

ይህንን የህዝብ ጥያቄ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ያመራው የሪያድ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማሕበር ሪያድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአይዟችሁ ተስፋን ይዞ ተመልሷል።

የማኅበሩ ሊቀ መንበር አቶ ሻወል ጌታሁን ለዶቸ ቬለ እንደተናገሩት መንግሥት ለውሳኔ ያመቸው ዘንድ  ወደ ሀገራቸው ጠቅለው መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ዝርዝር እና ተጨባጭ እውነታ ተዘጋጅቶ እንዲላክለት ጠይቋል። ስለሺ ሽብሩ ዝርዝር ዘገባ ከሪያድ ልኮልናል፤

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ