1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስዑዲ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ወደ የመን እየሸሹ ነዉ

ዓርብ፣ ሰኔ 16 2009

ስዑዲ አረብያ መንግሥት ሕጋዊ ያልሆኑ የዉጭ ሃገር ዜጎች ከሀገሪ ይዉጡልኝ ሲል ቀነ ገደብ ቢያስቀምጥም፤ በፍላጎት እንመለሳለን ብለዉ ከተነሱት ይልቅ የሆነዉን እንሁን ብለዉ እዝያዉ የተቀመጡት ኢትዮጵያዉያን ቁጥር በእጥፍ እንደሚበልጥ ተመለከተ።

https://p.dw.com/p/2fIHF
Illegale aus Äthiopien in Saudi-Arabien
ምስል DW/Sileshi Sibiru

Äthiopische Migranten in Saudi flüchteten nach Jemen*/MMT - MP3-Stereo

 

የስዑዲ አረብያ መንግሥት ያስረናል ብለዉ የሰጉ ሌሎች ዜጎች በበኩላቸዉ ወደ የመንን ወደመሳሰሉ ጎረቤት ሃገራት በእግር እየተመለሱ መሆኑም ታዉቋል። ከየመን ተነስተዉ ወደ ስዑዲ አረብያ በግር የሚጓዙት ኢትዮጵያዉያንም ጥቂት እንዳልሆኑ ነዉ የሚነገረዉ። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የገቡ ስምና አድራሻችን ከመመዝገቡ ሌላ የተፈየደልን ነገር የለም ሲሉ መልክት ያደረሱን አሉ ።

በስዑድ አረብያ ሕገወጥ ናችሁ ተብለዉ ወደሃገራቸዉ መመለስ የሚፈልጉ ኢትጵያዉያን በትራንስፖርት ችግር እየተጉላሉ መሆናቸዉ ተገለፀ። ጅዳ የሚኖረዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንደገለፀዉ በተለይ ትናንትና ከትናንት ወድያ በተለያዩ የበረራ አገልግሎት ሰጭዎች የአየር ትኬታቸዉን የገዙ ተመላሾች በአዉሮፕላን ጣንያ ሲንከራተቱ ነዉ የዋሉት።

ከዚህ ሌላ በኩል ክስ አለባችሁ ተብለዉ የመዉጫ መንገዱን ያጡ በየመን በኩል እንዉጣ እያሉ ወደ የመን እየተጓዙ መሆናቸዉን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ተናግሮአል። 

በስዑዲ አረብያ ሕገወጥ የተባሉ ኢትዮጵያዉያን ወደ የመን እየገቡ መሆናቸዉን ሰነዓ-የመን የሚገኘዉ ተባባሪ ዘጋቢያችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት ገልፆልናል። ግሩም እንደሚለዉ የሚገርመዉ ከየመን ወደ ስዑዲ አረብያም እገባለሁ ብሎ የሚጓዘዉ ኢትዮጵያዊ ጥቂት አይደለም።  የስዑዲ አረብያ መንግሥት ምናልባት ያወጣዉን የምሕረት አዋጅ ቀነ ቀጠሮ ሊያራዝም ይችላል ምናልባትም ነገ መግለጫ ይወጣል የሚለዉ ወሬ መናፈስ ከጀመረ አስር ቀናትን ደፈነ ያለን በጅዳ ነዋሪ የሆነዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በመቀጠል።

የስዑድ አረብያ ተመላሽ ኢትዮጵያዉያንን በተመለከተ በርካታ ተከታታዮቻችን ችግር ያሉትን በድምፅ መልክት ያካፍሉናል። በደቡብ ወሎ የሚገኙ አንድ አድማጫችን በአካባቢያቸዉ በሚገኘዉ የአዉቶቡስ መነሃርያ፤ ከስዑዲ ተመላሾችን አገባብ አይተዉ ነበር።  

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ