1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ የኦሮምያ ልዩ ጥቅሞችን የተመለከተ ረቂቅ አዋጅ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 20 2009

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዝርዝር ይዘት ይፋ ሆነ። የኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅምን ለማስጠበቅ የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በማጸደቅ ሂደት ላይ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/2fVQc
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

Q&A_spiacla Report über Oromia special interest - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖረውን ልዩ ጥቅምን በተመለከተ የተሰናዳውን ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላለፈ። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁ በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት አንቀፅ 49 ንኡስ አንቀጽ 5 የተቀመጡትን ከአገልግሎት አቅርቦት ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ልዩ ጥቅሞች ያላቸውን ማካተቱን አስታውቋል። በረቂቅ ህጉ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን ያስተሳስራሉ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ማዕከል በማድረግ የኦሮምያ ክልልን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ ያስችላሉ የተባሉ አንቀጾች መካተታቸውም ተዘግቧል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ስለ ረቂቅ አዋጁ ምንነት ባጭሩ ገልጿል።

 

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ