1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በ12 ከተሞች 86,000 ተፈናቃዮችን ለማስፈር ጥረት ላይ ነው

ረቡዕ፣ ጥር 30 2010

የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ የተፈናቀሉ 1.1 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረት ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የመረጃ ቋት (ReliefWeb) ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/2sHt8
Äthiopien Flüchtlinge vor ethnischer Gewalt
ምስል DW/J. Jeffrey

1 ሚሊዮን ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል

ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች የተፈናቀሉ 584,000 ዜጎች ወደ ቀደመ መንደራቸው መመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶታል። ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች በሌሎች አካባቢዎች የሚሰፍሩ ይሆናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ በ12 ከተሞች 86,000 ተፈናቃዮችን ለማስፈር ጥረት በማድረግ ላይ ነው። በተመረጡ 12 ከተሞች 12,000 የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት በድንበር ውዝግቡ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙባቸውን ቆሎጂ 1 እና ቆሎጂ 2 የተባሉ መጠለያዎች ለመዝጋት መወሰኑንም አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መፈናቀላቸውን ቀደም ብሎ መግለፁ አይዘነጋም። 
መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ